በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ገንዘብ ቢሮ የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ ለከተማ አስተዳደሩ መምሪያዎችና ጽ/ቤቶች አገልግሎት የሚሆን የተለያዩ ዕቃዎችን በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ገንዘብ ቢሮ የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ ለከተማ አስተዳደሩ መምሪያዎችና ጽ/ቤቶች አገልግሎት የሚሆን የተለያዩ ዕቃዎችን በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Sep 17, 2026)

ግልጽ ብሔራዊ የጨረታ ማስታወቂያ

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ገንዘብ ቢሮ የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ ለከተማ አስተዳደሩ መምሪያዎችና /ቤቶች አገልግሎት የሚሆን ሎት 01 የጽሕፈት መሣሪያዎች ሎት 02 ቋሚ እቃ/ፈርኒቸር/ ሎት 03 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ሎት 04 የፅዳት እቃዎች ሎት 05 ቶሎ ቶሎ የሚያልቁ የመኪና እቃዎች ሎት 06 የመኪና ጎማ ሎት 07 የመኪና ዘይት በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ የወጣውን ጨረታ በማየት ሰነዱን መግዛት የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

1. በዘርፉ በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፊኬት ያላቸው፡፡

2. የግዥ መጠኑ ከብር 500000 /አምስት መቶ ሽህ ብር/ በላይ ከሆነ ተጫራቾች የቫት ተመዝጋቢ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡

3. በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-2 ላይ የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን በጨረታ መክፈቻው ቀንና ሰአት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ከተራ ቁጥር 1-2 ላይ የተጠቀሱትን ኦርጅናል ሰነድ ይዘው መቅረብ አለባቸው፡፡

4. ተጫራቾች ከሎት 1 እስከ ሎት 7 ላሉት ለእያንዳንዳቸው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና CPO ብቻ የጠቅላላ ዋጋውን 1% ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡

5. ከተጫራቾች የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ጸንቶ መቆያ ጊዜ የጨረታው ዋጋ ጸንቶ ከሚቆይበት የመጨረሻ ቀን በኋላ ቢያንስ ለተጨማሪ 28 ቀናት ጸንቶ ይቆያል፡፡

6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር ብቻ/ ኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ 1 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 101 በመምጣት በመክፈል 07/1/2019 እስከ 16/01/2019 . ዘወትር በሥራ ሰዓት 1130 ድረስ መውሰድ ይችላሉ፡፡

7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናልና ኮፒ በተለያየ ፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ ኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ 1 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 114 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው ከወጣበት 07/1/2019 . እስከ 16/01/2019 . 1130 ድረስ መውሰድ ይችላሉ። የጨረታ ሳጥኑ 17/01/2019 . ከጠዋቱ 400 ታሽጎ በዚሁ ቀን 430 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በግልጽ ይከፈታል፡፡ ይሁን እንጂ የጨረታ መከፈቻ ቀኑ በዓል ከሆነና የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን ከላይ በተገለጸው የመክፈቻ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡

8. አሰፈላጊ ለሆኑ እቃዎች መምሪያው ሳምፕል የሚያቀርብ በመሆኑ ሳምፕሉን በጥንቃቄ በማየት እቃዎችን ማቅረብ ይጠበቅባችኋል፡፡

9. የጨረታው ውድድር የሚካሄደው በጥቅል ድምር ውጤት ስለሆነ የማይሞላ አይተም መኖር የለበትም፤ ያልተሞላ አይተም ከተገኘ ተጫራቾች ከጨረታ ውጭ ይደረጋሉ፡፡

10. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ ግልጽ ያልሆነ ነገር ሲያጋጥማቸው ጨረታውን ካወጣው አሠሪው መሥሪያ ቤት ጋር ከጨረታ መክፈቻ 5 /አምስት/ ቀን በፊት በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0913 509 999 ደውሎ መጠየቅ ይቻላሉ፡፡

11. የጨረታ ሰነዱ ላይ የድርጅቱ ማህተምና ፊርማ መደረግ ይኖርበታል፡፡ ጨረታ ሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለው ከጨረታ ውድድር ውጭ ያስደርጋል፡፡

12. ጨረታው ጸንቶ የሚቆይበት ጊዜ የጨረታ ሰነዱ ከተከፈተበት ጊዜ በኋላ 45 ቀናት ይሆናል፡፡

13. ጨረታውን ለማዛባት የሞከሩ ተጫራቾች ከጨረታ ውጭ እንደሚሆንና ለወደፊቱም በመሥሪያ ቤቱ ግዥ የማይሳተፍ እና ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚወረስ ይሆናል፡፡

14. ግዥ ፈጻሚው አካል ከአሸናፊው ተጫራች ጋር ውል ከመፈረሙ በፊት በአሸናፊው ተጫራች በውድድር የተገኘው ዋጋ ሳይቀየር በጨረታ ሰነዱ ላይ ከተገለጸው የአቅርቦት መጠን ላይ እስከ 20% ( ሃያ በመቶ ) መጨመር ወይም መቀነስ ይችላል፡፡

15. የጨረታ አሸናፊው ድርጅት ንብረቱን ኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ ንብረት ክፍል ድረስ በራሱ ወጭ ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡

16. መምሪያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ ለሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ገንዘብ ቢሮ የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *