የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ የSubmersible & Water Pump አቅርቦትና ገጠማ ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ የSubmersible & Water Pump አቅርቦትና ገጠማ ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Sep 19, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር DCE/S/125/2026

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ለድሬዳዋ ፌዴራል ፖሊስ ፕሮጀክት ግንባታ አገልግሎት የሚውሉ ዝርዝራቸው ከጨረታ ሰነዱ ጋር በተያያዘ የስራ ዝርዝር (Specification) መሰረት የ Submersible & Water Pump አቅርቦትና ገጠማ ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

.

የስራ ዝርዝር

የጨረታ ቁጥር

የጨረታ መዝጊያ ቀን

የጨረታ
መክፈቻ ቀን

1

Supply install, test & Commission Submersible & Water Pump

DCE/SF/125/2026

 

27/01/2019 .ከጠዋቱ 04:45

 

27/01/2019 .ከቀኑ 0500

 

ስለሆነም፡-

1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩ፤ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እና የታደሰ ታክስ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡

2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ CPO ወይም ከታወቀ ባንክ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (unconditional Bank Guarantee) ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

3. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ በጨረታ ሠነዱ በተጠቀሰው ብዛት እና ስፔስፍኬሽን መሠረት መሆን ይኖርበታል።

4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 200.00(ሁለት መቶ) በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት ቃሊቲ ቶታል ዝቅ ብሎ የቀድሞ መ.ኮ.ድ ግቢ በሚገኘው የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ዋናው መስሪያ ቤት የግዥ እና አቅርቦት አስተዳደር መምርያ መግዛት ይችላሉ።

5. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ሠነድ እና ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ እስከ መስከረም 27/2019ዓ.ም ከጠዋቱ 04፡45 ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

6. ጨረታው መስከረም 27/2019ዓ.ም ከጠዋቱ 05፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ ቡድን ቢሮ ይከፈታል።

7. አንድ ተጫራች ለአንድ ዕቃ መወዳደር የሚችለው በአንድ ዓይነት ሞዴል/ብራንድ/ ብቻ ነው። በአማራጭ የቀረበ ዋጋ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡

8. ኢንተርፕራይዙ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡- የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ
የቀጥታ ስልክ ቁጥር ቁጥር 0114-40-34-34/33 ማዞሪያ 0114-42-22-70/71/72
www.dce-et.com /Email:- info@dce-et.com 
ቃሊቲ ቶታል ዝቅ ብሎ የቀድሞ መ.ኮ.ድ ግቢ
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *