Addis Zemen (Sep 19, 2026)
የህንፃ ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የአለታ ወንዶ ከተማ አስተዳደር በመሳለሚያ ቀበሌ የሚገኘውን በአጠቃላይ የመሬቱ ስፋት 375 ካ/ሜ ላይ ያረፍውን G+2 ህንፃ በካሬ 12.3 ሜትር×16 ሜትር = 196.80 ካ/ሜ የሆነውን ህንፃ በመነሻ ዋጋ 17,443,550.33 በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
ስለዚህ ተጫራቾች፡-
- የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ ብር 100,000 ከታወቀ ባንክ /CPO/ማስያዝ የሚችል።
- ተጫራች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 400/አራት መቶ ብር/ ለአ ወ/ከ/ገ/ባ/ቅ/ጽ/ቤት በመክፈል እና ሰነዱን ከአለታ ወንዶ ከተማ ፋይናንስ ጽ/ቤት ግዥ ሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 08 በመውሰድ በተዘጋጀው የጨረታ ሠነዱ ላይ ዋጋውን በመሙላት ማስገባት ይችላል። ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ቅዳሜና እሁድን ጨምሮ ለተከታታይ ቀናት በ15 ለተከታታይ ቀናት ውስጥ በአ/ወ/ከ/ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ግቢ ውስጥ ባለው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በማስገባት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን የጨረታ ሳጥን በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዛው ቀን ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
የአለታ ወንዶ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት