የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን የቀላልና ከባድ ተሸከርካሪዎች ጥገና አገልግሎት/Service/ ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን የቀላልና ከባድ ተሸከርካሪዎች ጥገና አገልግሎት/Service/ ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Sep 19, 2026)

የቀላልና ከባድ ተሽከርካሪዎች ጥገና አገልግሎት ግዥ

የግልፅ ጨረታ ቁጥር ////001/2019

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን የቀላልና ከባድ ተሸከርካሪዎች ጥገና አገልግሎት/Service/ ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም በዘርፉ 2018/2019 የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፍቃድ እና ንግድ ምዝገባ ያላቸው፤የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣ በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት / የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ በድህረ ገፅ /Online/ የተመዘገቡ እንዲሁም ከደረጃ 2/ሁለት/ እስከ 4/አራት/ ድረስ ያሉ የጋራዥ ሰርቪስ አገልግሎት የሚሰጡ ማስረጃቸውን ኮፒና ኦርጅናል አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ ድርጅቶችና ግለሰቦች ቂርቆስ / ከተማ ወረዳ 01 ባንቢስ አካባቢ ግሪክ ትምህርት ቤት ፊት ለፊት ያለው ህንፃ ላይ 4ተኛ ፎቅ በኮርፖሬሽኑ የፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ቢሮ በመቅረብ የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ ለእያንዳንዱ የማይመለስ 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።

ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚሆን ብር 20,000.00 (ሃያ ሺህ ብር)በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (CPO) ወይንም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ከሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ጋር በማያያዝ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው የሚከፈተው መስከረም 25 ቀን 2019 . ከጠዋቱ 400 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ዕለት ከጠዋቱ 430 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ተወካዮች በተገኙበት በኮርፖሬሽኑ የመንግስት ግዥ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ 9 ፎቅ የቢሮ ቁጥር 901 ይከፈታል።

ኮርፖሬሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01

ባንቢስ አካባቢ ግሪክ /ቤት ፊት ለፊት በሚገኘው የቤቶች ልማት ህንፃ

ስልክ ቁጥር 0936 99 35 20/ 09 11 36 97 83

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *