በመከላከያ ኢንጅነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ 32 (ሰላሳ ሁለት) ስማርት ኤሌክትሪክ ፖል መብራቶችን ከነ ሙሉ አክሰሰሪው ለማሰራት በዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ በአገልግሎት ግዥ መፈፀም ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በመከላከያ ኢንጅነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ 32 (ሰላሳ ሁለት) ስማርት ኤሌክትሪክ ፖል መብራቶችን ከነ ሙሉ አክሰሰሪው ለማሰራት በዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ በአገልግሎት ግዥ መፈፀም ይፈልጋል


Addis Zemen (Sep 20, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ
ጨ.ሰ.ቁ፡- ቢ.ሞ.ቤ…/ብ.ግ.ጨ..ሰ/01/2018

በመከላከያ ኢንጅነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ የቢሾፍቱ ሞተር ቬህክልስ ኢንጅነሪንግ ኢንዱስትሪ በኢንዱስትሪው ውስጥ ያለ 32 (ሰላሳ ሁለት) ስማርት ኤሌክትሪክ ፖል መብራቶችን ከነ ሙሉ አክሰሰሪው ለማሰራት በዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ በአገልግሎት ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም ከታች የተገለፀውን ዝርዝር መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡

1) በዘርፍ የተሰማሩበት ህጋዊ የሆኑ በዘመኑ የታደሰ የንግድ ስራ ፍቃድ፤የዘመኑ ግብር የከፈሉ እና የግብር ከፋይ ተመዝጋቢ መሆኑን የሚያረጋግጥ ሰነድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) እና የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣

2) ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀናት በመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ በፋይናንስ በኩል የጨረታ ሰነዱን በብር 1,500 (አንድ ሺህ አምስት መቶ ብር) ከፍለው በመውሰድ ለጨረታ አስፈላጊ የሆኑ ሰነዶችን እና የምትወዳደሩበትን ዋጋ በመሙላት በፖስታ በማሸግ ኦርጅናል 01(አንድ) እና ኮፒ 01 (አንድ) ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፤

3) ማንኛውም ተጫራቾች በሚቀርቡት የጨረታ ሰነድ ላይ የተጫራቹ ወይም የሕጋዊ ወኪሉ ስም ፊርማና የድርጅቱ ማህተም መስፈር አለበት፡፡

4.ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ የተመሰከረለት የጨረታ ማስከበሪያ CPO፣በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

5) ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ በግልፅ በኢትዮጵያ ብር ነጠላ ዋጋና ጠቅላላ ዋጋ በዝርዝር ማስፈር አለባቸው፡፡ ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ ያካተተ መሆኑንና አለመሆኑ መገለፅ አለበት፡፡

6) አሸናፊ ተጫራቾች ውል ሲፈራረሙ የውል ማስከበሪያ ዋስትና (Perfomance Bond) ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% (አስር ከመቶ) በተመሰከረለት የባንክ ክፍያ ማዘዣ (CPO) ማቅረብ ይኖርባቸዋል እንዲሁም ውል ከተፈራረሙ በኋላ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ወዲያውኑ ይለቀቅላቸዋል፤

7) ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በኢንዱስትሪው ቅጥር ግቢ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፤ የጨረታ ሳጥኑ ከሚዘጋበት ሰዓት በኋላ የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡

8) ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ከዋናው ሰነድ ጋር በተያያዘው የዋጋ ማቅቢያ ሰንጠረዥ መሰረት በጥራትና በተቀመጠው ስፔስፊኬሽን መሠረት ሞልተው ማቅረብ አለባቸው፡፡

9) በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራች ከኢንዱስትሪው ጋር የሥራ አፈፃፀም ውል መፈራረም አለበት ውል ካልፈረመ ያስያዘው 2% (CPO) ተወርሶ ለኢንዱስትሪው ገቢ ይደረጋል :: 

10)ጨረታው የሚከፈተው ይህ የጨረታ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ተከታታይ የስራ ቀናት ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በእለቱ ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቢሾፍቱ ሞተር ቬህክልስ ኢንጅነሪንግ ኢንዱስትሪ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ቀኑ የበዓል ወይም የእረፍት ቀን ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን ከላይ በተገለፀው ሰዓት ይከፈታል፤

11)ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0994 521 556/0900 271 710 ደውለው መጠየቅ ይቻላል፤ 

12)ኢንዱስትሪው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው::

አድራሻ፡-ቢሾፍቱ ሞተር ቬህክልስ ኢንጅነሪንግ ኢንዱስትሪ ቢሾፍቱ/ደብረ ዘይት ስልክ ቁጥር ፡0994521556/0900271710

የመከላከያ ኢንጅነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *