Addis Zemen (Sep 20, 2026)
የላፍቶ የመ/ እና መለስተኛ ደረጃ/ት/ቤት የ2019 ዓ.ም
1ኛ ዙር (01/2019)
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ የላፍቶ የመ/ደ/ት/ቤት በ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት ሚያስፈልጉትን፡–
- ሎት 01 አላቂ የቢሮ ዕቃዎች
- ሎት 2 የደንብ ልብስ
- ሎት 3 አላቂ የጽዳት ዕቃዎች
- ሎት 04 አላቂ የላብራቶሪ ዕቃዎች
- ሎት 5 አላቂ የሕክምና ዕቃዎች
- ሎት 6 ቋሚ ዕቃዎች
- ሎት 07 አላቂ የትምህርት ዕቃዎች
- ሎት 08 የተለያዩ የጥገና ዕቃዎች
የላፍቶ የመ/ደረጃ ት/ቤት ለ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት አንደኛ ዙር ግልጽ ጨረታ ከላይ የተዘረዘሩትን ዕቃዎች ብቃት ባላቸውና በመስኩ የተሰማሩ ተጫራቾችን አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።
በዚህም መሰረት፡–
- በጨረታው ለመወዳደር ፍላጎት ያላቸውን ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የቲንና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የምስክሮ ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ የአንዱን ሎት የጠቅላላ ዋጋ 2 ፐርሰንት ከጨረታው ሰነዱን ሞልተው ሲመልሱ አብረው ማስገባት የሚችሉ፡–
- ተጫራቾች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ በተከታታይ በ10 የሥራ ቀናት የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በኣንድ ሎት በመክፈል በንፋስ ስልክ ክ/ ከተማ የላፍቶ የመ/ደ/ት ቤት ቢሮ ቁጥር 13 ግዥ ክፍል ቢሮ በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማስገባት ማህተም በማድረግ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለተከታታይ 10 የሥራ ቀናት ግዥ ከፍል ቢሮ ቁጥር 13 ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባችኋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 10ኛው ቀን በ10፡30 ተዘግቶና ታሽጎ በቀጣዩ ቀን ጠዋት 4፡30 ሰዓት በት/ቤቱ ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 13 ይከፈታል፡፡ የመክፈቻ ቀኑ እሁድና ቅዳሜ ወይም በበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ጨረታው ይከፈታል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሳጥኑ ከመከፈቱ በፊት ለተወዳደሩባቸው ሎት 01፡02፣03፣04፣05፣07፣08 ድረስ ላሎት ናሙና የዕቃውን መገለጫ/ ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን ለሎት 06 ግን በእስፔስፍኬሽኑ መሰረት ይሆናል።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን ዕቃዎች ለእያንዳንዱ ዕቃ ከቫት ጋር ያለውን ዋጋ ማስቀመጥ ይጠበቅባቸዋል።
- የዘገየ ጨረታና መከፈቻ ላይ ያልተነበበ ጨረታ ተቀባይነት የለውም።
- አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ዕቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ግዥ ፈፃሚው ላፍቶ የመ/ደ/ት ቤት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያና ጥያቄ ከታች ባለው አድራሻና ስልክ መጠቀም ይቻላል።
አድራሻ፡– ን/ስ ላፍቶ ወ.12 ላፍቶ በላይ ዳገቱን እንደጨረሱ በግራ በኩል ቁጥር 1 ኮንደሚኒየም ጎን ይገኛል።
ስልክ ቁጥር፡– 0913060108/0945310257
ማሳሰቢያ፡– የአነሰተኛና ጥቃቅን ተወዳዳሪዎች መወዳደር የሚችሉት በዘርፉ ባወጡት ንግድ ፈቃድ መሰረት ነው።
የላፍቶ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት