Addis Zemen (Sep 20, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 01/2019 ዓ.ም
በአራዳ ክ/ከተማ የዳግማዊ ሚኒሊክ ቅድመ አንደኛ ፣ አንደኛና መካከኛ ደረጃ ት/ቤት የፋይናንስ ቡድን የ2019 በጀት አመት 1ኛ ዙር ግልፅ ጨረታ የሚያስፈልገውን:-
- ሎት 1 የደንብ ልብስ
- ሎት-2 አላቂ የቢሮ ዕቃዎች
- ሎት-3 አላቂ የትምህርት እቃዎች
- ሎት-4 የተለያዩ መሳሪያዎች
- ሎት-5 የፕላንት ማሽነሪ እና መሣሪያ መግዣ
- ሎት-6 የደንብ ልብስ ስፌት
- ሎት-7 ቋሚና አላቂ ጽዳት እቃዎች
- ሎት-8 ህትመት
- ሎት-9 ለህንጻና ቁሳቁስ ለተገጣጣሚዎች መግዣ
- ሎት-10 ፕላንት ማሽነሪ ጥገና
- ሎት-11 ለህንጻና ቁሳቁስ ለተገጣጣሚዎች እድሳት ዕቃዎች መግዣ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም ተጫራቾች የሚከተሉትን ሁኔታዎች ቅድሚያ ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡
1. ተጫራቾች በተሰማሩበት የስራ መስክ የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸውና በዘርፉ የታደሰ የንግድ ምዝገባ ፍቃድ ማስረጃ ያላቸው TIN NO የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
2. በመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ዋናውንና አንድ ኮፒ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል እና በመንግስት ግዥ ያልታገዱ፡፡
3. ተጫራቾች የመጫረቻ ዋጋ ቫትን ጨምሮ በፖስታ አሽገው ማስታወቂያው ከወጣበት እለት ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10(አስር ) የስራ ቀናት ውስጥ ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚያገለግል ሎት 1፣2 እና 3 ብር 10,000.00(አስር -ሺህ ብር) ፣ሎት 4 እና 5 የመጫረቻ ዋጋ ብር 12,000.00(አስራ ሁለት ሺህ ብር) ፣ሎት 6 ፣7 እና 8 የመጫረቻ ዋጋ ብር 8,000.00(ስምንት ሺህ ብር) እና ሎት 9 ፣10 እና 11 የመጫረቻ ዋጋ ብር 9,000.00(ዘጠኝ ሺህ ብር በሕጋዊነት ከተረጋገጠ ባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
5. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የያዘ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት የጨረታ ሰነድ የፋይናንሻል ኦርጂናል እና እንዲሁም የቴክኒካል የኦርጅናል ኮፒ በመለየት ተሟልቶ በማሸግ ፊርማና ማህተም በማድረግ እንዲሁም ፖስታው ላይ አድራሻ ተጽፎ ቢሮ ቁጥር 10 (አስር) በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ት/ቤቱ ካዘጋጀው የዋጋ መሙያ ውጪ ሌላ ቅፅ መጠቀም ከጨረታ ውድድር ውጪ ያስደርጋል፡፡
6, ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት በአስራ አንደኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በእለቱ 4፡30 (አራት ተኩል) ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የመክፈቻ እለቱ በዓል ቅዳሜና እሁድ ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ይከፈታል፡፡
7. ናሙና ያልቀረበበት የዘገየ የጨረታ በመክፈት ሂደት ላይ ያልተነበበ ጨረታ እንዲሁም የጨረታ ሰነድ ተሟልቶ ያልመጣ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡ በጨረታ ሰነድ ክፍል 4.6.9 የተቀመጡት ግዴታዎች ከሰነዱ ጋር ተሟልተው ያላቀረቡ ተጫራቾች ተቀባይነት አይኖራቸውም፡፡
8. ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን 10% የውል ማስከበሪያ ማስያዣ እና ያሸነፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ግዢ ፈጻሚው መ/ቤት መጋዘን ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
9. በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ተቋማት እራሳቸው አምርተው ለገበያ በሚያቀርቡት እቃ እንደ ማነኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ አይጠበቅባቸውም፡፡
10. ስርዝ ድልዝ መረጃዎች ተቀባይነት የላቸውም፡፡ መስሪያ ቤቱ ለግዢው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ:-አራት ኪሎ ሚኒሊክ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ጎን ከሀገር አቀፍ ፈተናዎች ኤጀንሲ ገባ ብሎ እንገኛስን፡፡
የት/ቤቱ ፋይናንስ ቢሮ ስ.ቁ 011-23-28-66
የዳግማዊ ሚኒሊክ ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛና መካከኛ ደረጃ ት/ቤት