ብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ መካኒሳ ዋናዉ መስሪያ ቤት የሞላሰስ ማከማቻ ታንከር ኢፖክሲ የዉስጥ ሽፋን ሥራ የሚሰራ ድርጅት በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

ብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ መካኒሳ ዋናዉ መስሪያ ቤት የሞላሰስ ማከማቻ ታንከር ኢፖክሲ የዉስጥ ሽፋን ሥራ የሚሰራ ድርጅት በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል


2merkato.com (Sep 21, 2026)

የጨረታ ቁጥር 002/2019 ዓ.ም

ድርጅታችን መካኒሳ ዋናዉ መስሪያ ቤት የሞላሰስ ማከማቻ ታንከር ኢፖክሲ የዉስጥ ሽፋን ሥራ የሚሰራ ድርጅት በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።

በመሆኑም ተጫራቾች፡-

1. የታደሰ የንግድ ፍቃድና የዘመኑን ግብር ለመክፈላችሁ መረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤

2. የማይመለስ ቫትን አካቶ በብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሠነዱን መካኒሳ በሚገኘው ዋናው መ/ቤት ገንዘብ ቤት በመቅረብ መግዛት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፤

3. ፋይናንሻል እና ቴክኒካል ሰነድ ኦሪጅናል እና ፎቶ ኰፒ ለየብቻው በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ የሚቀርበው ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን አለመሆኑ በግልጽ መቀመጥ አለበት፤

4. ለጨረታ ዋስትና የሚሆን የሚያቀርቡትን አጠቃላይ ዋጋ 2% በሲፒኦ ለብቻው በኢንቨሎፕ በማሸግ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፤

5. ተጫራቾች የሚያስገቧቸውን ሠነዶች ጥቅምት 5 ቀን 2ዐ19 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡ዐዐ ሠዓት መካኒሳ በሚገኘው ዋናው መ/ቤት ግዥ ቢሮ 5ኛ ፎቅ ቁጥር 503 ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ጨረታው በዚያው ዕለት ከጠዋቱ 4፡15 ሠዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፤

6. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ

ፖ.ሣ.ቁ. 3516

ፋክስ 011 551 3299

Addis Ababa
Ethiopia


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *