በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ለወረዳው ግብርና ልማት ጽ/ቤት የእንስሳት መድሀኒቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ለወረዳው ግብርና ልማት ጽ/ቤት የእንስሳት መድሀኒቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Sep 21, 2026)

ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ግልፅ 
የጨረታ ማስታወቂያ

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ለወረዳው ግብርና ልማት ጽ/ቤት የእንስሳት መድሀኒቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ ከዚህ በታች መስፈርቱን የምታሟሉ ተጫራቾች ማለትም።

  1. ሎት1 የእንስሳት መድሀኒት

1. በዘርፉ ህጋዊ ፍቃድ ያላችሁና የዘመኑ ግብር በመክፈል ፍቃድ ያደሳችሁ።

2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር(ቲን) ማቅረብ የሚችሉ።

3. በመድሀኒት አቅራቢነት የተመዘገቡበት የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።

4. ተጫራቾች የሚወዳደሩበት ከጠቅላላ ገንዘብ 20,000 (ሀያ ሺህ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠለት ሲፒኦ (ጥሬ ገንዘብ) በእዣ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ስም ማቅረብ አለባቸው።

5. ተጫራቾች አሸናፊ የሆኑባቸውን መድሀኒቶች እዣ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት መጋዘን ድረስ አጠቃላይ በአንድ ጊዜ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።

6. ተጫራቾች የጨረታው ዝርዝር የያዘ ዶክመንት ለመግዛት የሚያስችል የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ሰነዳቸው ፋይናንስ ጽ/ቤት ግ/ን/አስተዳደር የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 03 መውሰድ ትችላላችሁ።

7. ተጫራቾች ማሸነፋቸው ከተገለፀ ቀን ጀምሮ በ7 የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፈበት ጠቅላላ ዋጋ 10% /በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ በማስያዝ ውል መፈፀም አለባቸው።

8. ተጫራቾች በጨረታው ማሸነፋቸው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ7 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ውል ማስከበርያ አሰርቶ ውል ካልፈፀሙ መስርያ ቤቱ የጨረታ ማስከበርያውን የመውረስ መብት አለው።

9. ተጫራቾች የጨረታው ሰነዳቸው አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ በታሸገ ፖስታ በማድረግ ጨረታው ከወጣበት ቀን 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ማለትም ቅዳሜና እሁድ እዲሁም የበዓል ቀናት ጨምሮ አየር ላይ ይውላል። ጨረታው በ16ኛ ቀን ከቀኑ 8፡00 ድረስ ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይችላሉ።

10. ጨረታው በ16 ቀን 8፡00 ታሽጎ በዚሁ እለት ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ነገርግን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው አለመገኘት ጨረታው ከመክፈት አያስተጓጉለውም።

11. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

12. ተጫራቾች የተጫረቱባቸው መድሀኒቶች ሳምፕል ማቅረብ አለባቸው።

13. መድሀኒቶቹ ሁሉንም እስከ ፋይናንስ ማስረከብ ድረስ ያለው ወጪ ከተወዳዳሪው ይሆናል።

14. አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለ60 ቀናት ፀንቶ ይቆያል።

ማሳሰቢያ፦ ወረዳው በጉራጌ ዞን ከወልቂጤ ከተማ 42 ኪ.ሜ ከአዲስ አበባ 197 ኪ.ሜ ላይ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ በስ.ቁ 09-23-51-95-14/ 09 13-37-12-45/ 09-11-07-70-93

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በጉራጌ ዞን
እዣ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት /ገና/


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *