በአሽ/ተሽ/ፈ/ቁ//ባለስልጣን/ አቃቂ ቃሊቲ ቅ/ጽ/ቤት የተለያዩ እቃዎቸን መግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በአሽ/ተሽ/ፈ/ቁ//ባለስልጣን/ አቃቂ ቃሊቲ ቅ/ጽ/ቤት የተለያዩ እቃዎቸን መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Sep 22, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 01/2019 ዓ.ም

በአሽ/ተሽ/ፈ/ቁ//ባለስልጣን/ አቃቂ ቃሊቲ ቅ/ጽ/ቤት አገልግሎት የሚውሉ የደንብ ልብስ፤ አላቂ የቢሮ እቃዎችንና የተለያዩ የቢሮ ዕቃዎች የጥገና ማለትም፣

ሎት 1 የደንብ ልብስ፣ ሎት 2. አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎች፣ ሎት 3. የጽዳት ዕቃዎች፣ ሎት 4 የመኪና እቃዎች፣ ሎት 5. ልዩ ልዩ መሳሪያዎች፣ ሎት 6. ስካነር ኮምፒውተር የቅሬታ ማሽን፤ ፋርጎ ፕሪንተር ቴሌቭዥን፤ ፋን፤ ፎቶ ኮፒ ማሽን፤ ፕሪንተር፣ ጠረጴዛ፤ ወንበርና የኤሌክትሪክ መስመሮችና መብራቶችን የጥገና ስራ ለማሰራት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በዚሁ መሰረት ከታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መሳተፍ ይችላሉ።

1. ተጫራቾች በመስኩ የተሰማሩ፣ ህጋዊ እና የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የኢፌድሪ የገንዘብ ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ባዘጋጀው የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡና የተ.እ.ታ ተመዝጋቢዎች ለመሆናቸው ኮፒ ማስረጃ እና Tin No ሰርተፍኬት ኮፒ ማቅረብ አለባቸው።

2. ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10/አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት ከሰኞ እስከ አርብ ከጥዋቱ 2፡00 – 10፡00 ሰአትና ቅዳሜ ግማሽ ቀን ጨምሮ ቢሮ ቁጥር 42 በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡

3. ተጫራቾች በገዙት የጨረታ ሰነድ መሰረት የሚወዳደሩበትን ዋጋ በዋጋ ማቅረቢያ/financial ሰነድ፣ እንዲሁም አስፈላጊ ቴክኒካል ሰነዶችን ለየብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ በመለየት ኦርጂናልና ኮፒውን ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10/አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት ቢሮ ቁጥር 31 በመቅረብ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚጫረቱበትን ለእያንዳንዱ ሎት በተናጥል 3,000.00/ ሶስት ሺ/ ብር በባንክ የተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ/CPO/ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

5. ተጫራቾች የመጫረቻ ዋጋቸውን መ/ቤቱ በሰጣቸው ሰነድ ላይ መሙላት እና በእያንዳንዱ የመጫረቻ ሰነዳቸው ላይ ፊርማ መፈረም እና የድርጅቱን ማህተም ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።

6. ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች ናሙና እንዲቀርብ ለተጠየቀባቸው ዕቃዎች ጨረታ ከመክፈቻ ቀን በፊት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

7. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ፣ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰአት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡30 ሰአት ላይ ይከፈታል።

8. ተጫራቾች ውሉን ሲዋዋሉ ያሸነፉበትን የጠቅላላ ዋጋውን 10% በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ/CPO/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

9. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 09 22 45 04 40/ 09 10 70 49 72 ደውሎ መጠየቅ ወይም ቃሊቲ ማሰልጠኛ ግቢ ውስጥ በር 3 ከሚገኘው ቅ/ጽ/ቤታችን ቢሮ ቁጥር 3 በአካል በመቅረብ መጠየቅ ይቻላል።

የአሸ/ተሸ/ፈ/ቁ/ ባለስልጣን አቃቂ ቃሊቲ ቅ/ጽ/ቤት