በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የብርሃን አይነስውራን አዳሪ ት/ቤት የተለያዩ እቃዎችን ግዥ መፈጸም ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የብርሃን አይነስውራን አዳሪ ት/ቤት የተለያዩ እቃዎችን ግዥ መፈጸም ይፈልጋል


Addis Zemen (Sep 21, 2026)

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የብርሃን አይነስውራን አዳሪ ት/ቤት የ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት በ1ኛ ዙር በግልፅ ጨረታ የሚገዙ ዕቃዎች, ብቃት ያላቸውንና በመስኩ የተሰማሩ ተጫራቾችን አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡ ፡

በዚህ መሰረት

1.በጨረታው ለመወዳደር ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው ፤ የዘመኑን ግብር የከፈለ በመንግስት ግ/ን/አስ/ኤጀነሲ ድህረ ገጽ ላይ በአቅራቢዎች ምዝገባ ዝርዝር የተመዘገቡ ፤ የቲን እና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።

2.ተጫራቾች የጨረታው ማስከበሪያ ፤(ሎት1) የቋሚ እቃዎች 30,000ብር፣(ሎት2) አላቂ የቢሮ ዕቃዎች 20,000 ብር ፤ (ሎት3) ደንብ ልብስ 15,000 ብር፤(ሎት4) የሕትመት 5,000ብር፣(ሎት5.የፅዳት እቃዎች 15,000 ብር፤(ሎት6) የጥገና ዕቃዎች 10,000ብር፥(ሎት7) የመፃፍ ግዥ 5,000 ብር (ሎት8) የመኪና መለዋወጫ እቃዎች ብር 5,000 ብር (ሎት 9) የህክምና እቃዎች 10,000 ብር በባንክ የተረጋገጠ (CPO)በታሸገ ፖስታ ብቻውን ማቅረብ አለባቸው፡፡ በጥቃቅንና አነስተኛ ከሆነ በኦዲት በተረጋገጠ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡

3.ተጫራቾች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት አንስቶ ተከታታይ 10 የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከ ወረዳ 8 አከባቢ የብርሃን አይነ ስውራን አዳሪ ት/ቤት ቢሮ ቁጥር 8 በመምጣት የጨረታ ሰነዱን በቲሌግራም እና በፍላሽ መውሰድ ይችላሉ፡፡የጨረታ ሰነዱ ፕሪንት ተደርጎ ዋጋዉ ሰነዱ ላይ ተሞልቶ ሙሉውን ሰነድ ይመለሳል፡፡

4.የመጫረቻ ሰነዳቸውን ኦርጅናል፣ኮፒ፣ቴክኒካል እና ሲፒዮ፤ በ4 ፖስታ ለየብቻ ታሸጎ የሚመለስ ይሆናል ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት ፋይናንስና ግዥ ቢሮ ቁጥር 8 ለጫረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

5.ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ11ኛው ቀን በ04፡00 ሰዓት ታሽጎ በ11ኛው ቀን ልክ በ4፡ 30 ሰዓት በት/ቤቱ ቢሮ ቁጥር 8 ይከፈታል፡፡የመክፈቻ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ ከሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ ይከፈታል፡፡

6.ተጫራቾች የጨረታ ሳጥን ከመከፈቱ በፊት ለተወዳደሩባቸው ሎት2 ፣ሎት3፣ ሎት4 ፤ሎት5፤ሎት6፤ሎት7፤ ሎት8፤እና ሎት 9 ናሙና ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን ለ ሎት1 የፎቶ ናሙና እና የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ማለትም ቋሚ እቃ በት/ቤቱ በአካል ሚመጡ ሲሆን ት/ቤቱ ባዘጋጀው ሰነዱ ላይ ስፒስፊክሽን መሰረት እቃዎችን ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

7.ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን እቃዎች ለእያንዳንዱ ከቫት ጋር ያለውን ዋጋ ማስቀመጥ ይጠበቅባቸዋል፡፡

8.የዘገየ ጨረታና በጨረታ መክፈቻ ላይ ያልተነበበ ጨረታ ተቀባይነት የለውም፡፡

9.አሸናፊ ተጨራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ግዥ ፈጻሚ መስሪያቤቱ ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፨

10.መስሪያቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጫረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡- በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ጀርባ / የነገዋ የሴቶች ተሃድሶ ማዕከል በስተግራ በኩል ወደ ስላሴ ቤ/ክርስቲያን ወረድ ብሎ የብርሃን ዓይነ ስውራን አዳሪ ት/ ቤት ቢሮ ቁጥር 8

ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር-0921 762 594/0910 220 199
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የብርሃን አይነስውራን አዳሪ ት/ቤት