Addis Zemen (Sep 21, 2026)
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 008/2019 ዓ ም
በኮልፌ ቀራኒዮ ከፍል ከተማ በወረዳ 07 የጄኔራል ዋቆ ጉቱ 1ኛ ደረጃ ቁጥር -1 ት/ ቤት ፋይንስ ክፍል በ2019 በጀት ዓመት የተዘረዛሩትን እቃዎች የግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
- ሎት 1. ልዩ ልዩ አላቂ የቢሮ እና ትምህርት ፅቃዎች
- ሎት 2. የፅዳት እቃዎች
- ሎት 3. ማስተንግዶ እቃዎች
- ሎት 4. ደንብ ልብስ
- ሎት 5. የህትመት ስራ
- ሎት 6. ቋሚ እቃዎች
- ሎት7 . ኤክትሮኒክስ ጥጋና ስራ
ስለዚህ በጨረታው መሳተፍ ለሚፈላጉ ተጫራቾች /ድርጅቶች/ በዚሁ መሰረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርት የምታሟሉ ድርጅቶች በጨረታ እንዲተሳተፉ ተጋብዘዋል ።
1. በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የአቅራቢዎች ምዝገባ እና የምስክር ወረቀት ያላቸው እና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ።
2. ለመጫረት የሚያበቃ መረጃ መቅረብ የሚችሉ።
3. ተጫራቾችማስታውቂያ ከወጣበትቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት 2፡30 እስከ 6፡30 ከሰዓት ደግሞ 7፡30 እስከ 11፡30 የስራ ቀናት ውስጥ በጄኔራል ዋቆ ጉቱ 1ኛ ደረጃ ቁጥር 1 ት/ቤት ግዥ ክፍል መመዝገብ ትችላላችሁ ፡፡
4. ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ለመግዛት ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ 300 ብር /ሶስት መቶ ብር/ ከፍለው መውሰድ ትችላለችሁ።
5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በተረጋገጠ ሲፒኦ/በአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ በኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ ወረዳ 07 ት/ጽ/ቤት የጄኔራል ዋቆ ጉቱ 1ኛ ደረጃ እና መካከለኛ ደረጃ ቁጥር 1 ት/ቤት ስም ማስጋበት/ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ሎት 1. 16000 ብር
- ሎት 2 . 8000 ብር
- ሎት 3 . 2000 ብር
- ሎት 4 . 18000 ብር
- ሎት 5 . 4000 ብር
- ሎት 6 . 12000 ብር
- ሎት 7. 8000 ብር
6. ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ላይ ታሽጎ በዕለቱ የስራ ሰዓት 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎች በተጋኙበት ቦታ ይከፋታል ፤ነገር ግን የመከፈቻው ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀናት ይካፈታል።
7. ተጫራቾች በሚወዳዲሩበት ዕቃዎች በሙሉ ጨረታው ከመከፈቱ በፈት ናሙና ማቅረብ አለባቸው።
8. አንድ ተጫራች ሌላው በሰጠው ዋጋ ተነስቶ ማቅረብ አይችልም።
9. ተጫራቾች በገዙት ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ መሙያ ላይ ቫትን ጨምሮ በግልጽ መሙላት አለባቸው።
10. ት/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
11. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፈባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ግዥ ፈፃሚ መስሪያ ቤት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
12. ዕቃውን ሲያስገቡ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 6፡00 ሰዓት ሲሆን ከሰዓት ደግሞ 7፡30 እስከ 9፡30 ድርስ መሆኑን እያስወቅን፤ ከተጠቀሰው ሰዓት ውጭ የማናስተናግድ መሆኑን እንገልፃለን።
13. ጥቃቅንና አነስተኛ ከተደራጁበት መስሪያ ቤት ደብዳቤ ይዘው ሲቀርቡ የጨረታውን ሰነድ በነፃ መውሰድ ይችላሉ።
14. መ/ቤቱ የሚያጫርታቸውን እቃ በብዛት እንዳ አስፈለጊነቱ 20% ጨምሮ ወይም ቀንሶ ማዘዝ ይችላል።
15. ጨረታው ከተዘጋ በኃላ የሚመጣ የተጫራች ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
አድራሻ፡– ጄኔራል ዋቆ ጉቱ 1ኛ ደረጃ ቁጥር 1 ት/ቤት አዲስ ተስፋ ት/ ቤት ፊት ለፊት
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ 0921 210 112 / 0952 141 971
በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ በወረዳ 07 የጄኔራል ዋቆ ጉቱ 1ኛ ደረጃ ቁጥር– 1 ት/ቤት