Addis Zemen (Sep 22, 2026)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በደ/ምዕ/ኢት/ያ/ሕ/ክ/መ/የኮንታ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ለኮንታዞን ትምህርት እና ጤና መምሪያዎች የተለያዩ ግንባታዎችን በሎት 1 ባከ ሰዳ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት አንድ ብሎክ፣ሎት 2 ጭዳ ቀድሞ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ሙሉ ጥገና፣ ሎት 3 አመያ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ማስፋፊያ፣ ሎት 4 ጭዳ 2ኛ ደረጃ መማሪያ አንድ ብሎክ፣ ሎት 5 ኮይሻ አንደኛ ደረጃ አንድ መማሪያ ብሎክ፣ ሎት 6 ጨበራ ሻሾ ጤና ጣቢያ ውስጥ መፀዳጃ ቤት፣ የእንግዴ ልጅ መቅበሪያ እና ደረቅ ቆሻሻ ማቃጠያ ጉድጎድ ሎት 7 ጨበራ ሻሾ ጤና ጣቢያ ውስጥ የጥበቃ ቤትና ዙሪያ አጥር ግንባታ ሎት 8 ጨበራ ሻሾ ጤና ጣቢያ ውስጥ አንድ ተጨማሪ ክፍል ለመዝገብ ቤት፣ ካርድ ክፍል እና ካሸር ክፍል ግንባታ በ2019 በጀት ዓመት በካፒታል በጀት ሲሆን ሎት 1፣ ሎት 2ና ሎት 3GC/BC ደረጃ 5 እና ከዛ በላይ እና ሎት 4፣ ሎት 5፣ሎት 6፣ ሎት 7ና ሎት 8 በደረጃ 9 3GC/BC በአካባቢ የተደራጀ ማህበራት ህጋዊ ፍቃድ ያላቸው ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ለማስገንባት ይፈልጋል።
በዚሁ መሠረት ለመጫረት የምትፈልጉት፡–
1. በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ፤2/ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት 3/ ግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር 4/ የመንግሥት ግዥ ላይ አቅራቢነት ሰርተፊኬት 5/ ተጨማሪ እሴት ታክስ 6/ የታደሰ ብቃት ማረጋገጫ ምዝገባ ምስክር ወረቀት 7/ የግብር ዘመኑ ከዕዳ ነፃ መሆኑን የሚያረጋግጥ ታክስ ክሊራንስ 8/መልካም ሥራ አፈፃፀም የ2016 ወይም 2017 ዓ/ም ወይም 2018 ዓ.ም ኮፒ ማቅረብ የሚችል፤ በ2018 ዓም ፍቃድ ያውጡትን የመልካም ሥራ አፈፃፀም አይመለከታቸውም።
2/ተጫራቾች ሎት 1፣ ሎት 2 እና ሎት 3 ለጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ (CPO) 300,000 (ሦስት መቶ ሺህ ብር) እና ሎት4 ሎት 5 ሎት 6 ሎት7ና ሎት 8 ለጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ (CPO) 150,000 (አንድ መቶ ሃምሳ ሺህ) ብር ብቻ ከታወቀ ባንክ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
3/ ተጫራቾች እያንዳንዱ ሎት 1፣ ሎት 2 እና ሎት 3 ይህ ጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ቅዳሜ እና እሁድን ጨምሮ 21ኛው ቀን ድረስ እና እያንድንዱ ሎት4 ሎት 5 ሎት6 ሎት እና ሎት 8 15ኛ ቀን ድረስ በኮንታ ዞን ፋይናንስ መምሪያ የጨረታ ዶክመንት በመግዛት እና በዋጋ ማቅረቢያ በመሙላት ቴክኒካል ኦርጅናል 1፣ እና ኮፒ 1 ፋይናንሻል ኦርጂናል1 እና ኮፒ2 በድምሩ 5 ፖስታ የድርጅታችሁን ማህተም በማድረግ በጨረታ ፖስታ በማሸግ በኮንታ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ለዚሁ ዓላማ በብጋው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
4. በተራ ቁጥር ቁጥር 9 መሠረት ሎት 11፣ ሎት 2 እና ሎት 3 የጨረታ ሣጥን የሚከፈተው በ22ኛው ቀን እና ሎት 4፣ ሎት 5፣ ሎት6፣ ሎት 7 እና ሎት 8 የጨረታ ሣጥን የሚከፈተው 16ኛ ቀን የመንግስት ሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው በሥራ ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮንታ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ይከፈታል።
5. ተጫራቾች የጨረታ ዶክመንት የማይመለስ 500 አምስት መቶ ብር ብቻ በመክፈል ከኮንታ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 9 መውሰድ ይኖርባቸዋል።
6. በዚሁ የጨረታ ማስታወቂያ ላይ የተገለፁት መስፈርቶችን የማያሟላ ተጫራች ለቴክኒካል ግምገማ የማያልፍ ሲሆን መስፈርቱን ያሟላ ተጫራች ወደ ቴክኒካል ግምገማ የሚቀርብ ይሆናል።
7. በዚሁ በቅድመ ግምገማው ላይ ያልተገለፁ መስፈርቶች በዋናው ተጫራቾች መመሪያ ላይ ተመላክቷል።
8. ሂሳብ ስህተት ከተነበበው ጠ/ዋጋ ከ5% በላይ በሆነ መጠን የሚበልጥ ወይም የሚያንስ ከሆነ በግዥ መመሪያ ተግባራዊ ይደረጋል፡፡ ተጨማሪ እሴት ታክስ 7.5% እና የውዝሆልዲንግ 3% ከፍያ ስርዓት ተግባራዊ ይደረጋል።
መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ፡– ማብራሪያ በስልክ ቁጥር፡– 047 227 0007 / 0917 388 691/ 0917 161 785 / 0935 138 008 መደወል ይችላሉ።
በደ/ምዕ/ኢት/ያ/ሕ/ክ/መ/የኮንታ ዞን ፋይናንስ መምሪያ