ትንቢተ ኤርሚያስ ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት የተለያዩ እቃዎችን መግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

ትንቢተ ኤርሚያስ ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት የተለያዩ እቃዎችን መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Sep 22, 2026)

አንደኛ ዙር ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 001/2019

ኮ/ቀ/ክ/ከ /ወ/09 ትንቢተ ኤርሚያስ ቅድመ አንደኛ፤ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት 2019 በጀት አመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ሎቶች፡

የሎት ዝርዝር

 

የእቃው አይነት

 

የተጠየቀው የጨረታ ማስከበሪያ

ሎት 1

ደንብ ልብስ

 

16,500 ብር

 

ሎት2

አላቂ የጽፈት እቃዎች

 

7,500 ብር

 

ሎት3

አላቂ የጽዳት እቃዎች

 

13,500 ብር

 

ሎት4

አላቂ የትምህርት እቃዎች

 

16.000 ብር

 

ሎት5

ለህንፃ ፣ለቁሳቁስ እና ተገጣጣሚ  እቃዎች

 

9,000 ብር

 

ሎት6

ቋሚ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች

 

10,000 ብር

 

ሎት7

ጥገና እቃዎች

 

5,000 ብር

 

ሎት8

ጥገና ሥራ

 

6,000 ብር

 

ሎት9

ህትመት

 

1,500 ብር

 

ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

  1. የከፈሉበትና የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችል የንግድ መስክ ያለው።
  2. በአቅራቢነት የተመዘገበበትን ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል፣ ቫት ተመዝገቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ።
  3. ተጫራቾች ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር በተራ ቁጥር 1እና 2 ላይ የተገለጹትን ሰነዶች ኮፒ አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
  4. ተጫራቾች የጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 የስራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡30 ድረስ በትንቢተ ኤርሚያስ ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛና መካከስኛ ደረጃ ት/ ቤት የማይመስስ ለእያንዳንዱ ሎት ብር 300(ሶስት መቶብር) በመክፍል የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ መውሰድ ይችላሉ።
  5. ተጫራቾች በገዙት ሰነድ የዋጋ ማቅረቢያ ላይ በመሙላት በመፈረም የተሟላ አድራሻ የሚገልጽ ህጋዊ ማህተም ያረፈበት ከዚያ በላይ የተጠቀሰው የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ለእያንዳንዳቸው ሎት ሲፒ ኦ ሰነድ ጋር ማያያዝ ይኖርባቸዋል።
  6. ማንኛውም ተጫራች የሚጫረትበትን እቃ የቫት ዋጋ ጨምሮ እቃውን ዝርዝር ማስገባት ይኖርበታል።
  7. ማንኛውም ተጫራች ያሸነፈበትን ህጋዊ ደረሰኝ ማቅረብ ይኖርበታል።
  8. በታሽገ ኤንቨሎፕ ዋናው እና ፎቶኮፒ በተለያየ ባሉት 10  የስራ ቀናት ውስጥ ግዥ ቢሮ በግንባር ቀርቦ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ዋናው ኤንቨሎፕ በየሎቱ በማድረገ ይኖርባቸዋል።
  9.  በ11ኛ ቀን ከጠዋቱ 3:30 የሚታሽግ ይሆንና 4፡00 ሰዓት በዚሁ ቀን የታሽገው የጨረታ  ሳጥን ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
  10. ት/ቤት በጨረታው ሰነድ ላይ ከቀረቡ እቃዎች ብዛት 20% የመቀነስ ወይም የመጨመር  መብት አለው።
  11. አሸናፊው ተጫራች እንደታወቀ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% የጨረታ ዋስትና በባንከ በተረጋገጠ ሲፒዩ ማስያዝ ይኖርበታል።
  12. አሸናፊው መሆኑን ከተገለጸበት 10 ቀን ውስጥ ቀርቦ ውል ካልተፈራረመ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይሆናል።
  13. ተጫራቾች በሰነዱ ላይ ናሙና እንዲያቀርቡ ለተጠየቁባቸው እቃዎች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ናሙና ማቅርብ አለባቸው።
  14. ተጫራቾች ያሽነፉበትን እቃዎች ውል ከተዋዋሉበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የስራ ቀናት ውስጥ በራሳቸው ትራንስፖርት እስከ ት/ቤቱ እቃ ግምጃ ቤት ድረስ ገቢ ማድረግ እና ሞዱል 19 ማስቆረጥ አለባቸው።
  15. ት/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ  የተጠበቀ ነ።
  16. በጥቃቅን እና አነስተኛ የተደራጅ ከሆነ የተደራጁበትን የስራ መስክ (ዘርፍ)የሚገልጽ በጨረታው የሚያሳትፍ የድጋፍ  ደብዳቤ በጽ/ቤቱ ኃላፊ ፊርማ እና ማህተም የተረጋገጠ ማቅረብ የሚችል።

አድራሻ – አ/አ/ኮ/ቀ/ክ/ከተማ ወረዳ 9 ትንቢተ ኤርሚያስ ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ከጋና ሌምባሲ ፊት ለፊት ባለው መንገድ ገባ ብሎ ወይም ቻይና ኤምባሲ አካባቢ ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 011 320 1000 / 011 383 5257

ኮ/ቀ/ክ/ከ /ወ/09 ትንቢተ ኤርሚያስ ቅድመ አንደኛ፤ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት