ኦሮሚያ ስቴት ዩኒቨርሲቲ ሰበታ ካምፓስ ለ2019 በጀት ዓመት ለትምህርት አገልግሎት የሚውሉ የጽሕፈት መሣሪያዎች፣ የጽዳት ዕቃዎች፣ አላቂ ዕቃዎች፣ የደንብ ልብሶች፣ የመኪና ጎማዎችን፣ ኤሌክትሮኒክስ እና ፈርኒቸር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

ኦሮሚያ ስቴት ዩኒቨርሲቲ ሰበታ ካምፓስ ለ2019 በጀት ዓመት ለትምህርት አገልግሎት የሚውሉ የጽሕፈት መሣሪያዎች፣ የጽዳት ዕቃዎች፣ አላቂ ዕቃዎች፣ የደንብ ልብሶች፣ የመኪና ጎማዎችን፣ ኤሌክትሮኒክስ እና ፈርኒቸር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Sep 21, 2026)

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር 002/2019

ኦሮሚያ ስቴት ዩኒቨርሲቲ ሰበታ ካምፓስ 2019 በጀት ዓመት ለትምህርት አገልግሎት የሚውሉ ሎት1, የጽሕፈት መሣሪያዎች፤ የጽዳት ዕቃዎች፣ አላቂ ዕቃዎች፣ የደንብ ልብሶች፣ ሎት 2 የመኪና ጎማዎችን፤ ኤሌክትሮኒክስ እና ፈርኒቸር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ በጨረታው መወዳደር የምትፈልጉ ከዚህ በታች የተዘረዘረውን መስፈርት የምተሟሉ ድርጅቶችና ግለሰቦች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ይገልጻል፡፡

1. ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና እንዲሁም የሚፈለግባቸውን የዘመኑን ግብር አጠናቀው ስለመክፈላቸው በቂ ማስረጃ (ክሊራንስ) ከሚመለከተው አካል ማቅረብ የሚችሉ፡፡

2. ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ለእያንዳንዱ ሎቶች የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ከካምፓሱ ሂሳብና በጀት ቢሮ ቁጥር 12B መውሰድ ይችላሉ፡፡

3. ተጫራቾች የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት እና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (ቲን) ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስት ለእያንዳንዱ ሎቶች በተዘጋጀው ሰነድ ብር 30,000.00 (ሰላሳ ሺህ ብር) በባንክ በተመሰከረለት CPO ብቻ ኦሮሚያ ስቴት ዩንቨርሲቲ ሰበታ ካምፓስ ስም አዘጋጅተው ከመጫረቻ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

5. ተጫራቾች የሚያቀርቡት CPO በጀርባው የባንኩን ማህተም እና ስልክ ቁጥር ከሌለው ተቀባይነት አይኖረውም፡፡

6. ተጫራቾች ሰነዱን ከገዙ በኋላ የሚሸጡበትን ዋጋ ቫትን ጨምሮ (15%) በመጥቀስ በታሸገ ኤንቨሎፕ ኦሪጅናል እና ኮፒ ሰነድ ለየብቻ በማሸግ በተባለው ቀን ውስጥ ለጨረታው በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

7. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ቫት ተመዝጋቢ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡

8. ለጨረታ በሚያቀርቡት በእያንዳንዱ የሰነዱ ገጽ ላይ የድርጅቱን ስምና አድራሻ የሚገልጽ ሕጋዊ ማህተምና ፊርማ ማስፈር አለበት፡፡

9. ተጫራቾች ያሸነፉትን እቃዎች በራሱ ትራንስፖርት መሥሪያ ቤቱ ባዘጋጀው ቦታ ድረስ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡

10. ተጫራቾች ያሸነፉትን ዕቃዎች ገቢ የሚሆነው አስፈላጊውን ጥራት ማሟላቱን በባለሙያ እና ጥራት አጣሪ ኮሚቴ ሲረጋገጥ ብቻ ይሆናል፡፡

11. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዕቃ በመጋዘን ቀድመው ማከማቸት ይኖርባቸዋል፡፡

12. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዕቃ የሎት አንድ(1) ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ናሙናውን ማቅረብ አለባቸው፡

13. የጨረታው ሰነድ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 የሥራ ቀናት የሚሸጥ ሆኖ 16ኛው ከረፋዱ 400 ሰዓት ተዘግቶ በተጠቀሰው ቀን 430 የሚከፈት ይሆናል፡፡

14. በዚህ ጨረታ አሸናፊ የሆነ ተጫራች (ድርጅት) የሚያስገባውን ዕቃ ዋጋ ከመቶ አስር 10 ፐርሰንት የማስያዝ ግዴታ አለበት፡፡

15. ከላይ የተገለጸው የመክፈቻ ቀን በዓል ወይንም የሰንበት ቀን ላይ ከዋለ ጨረታው የሚከፈተው በቀጣዩ የሥራ ቀን ይሆናል፡፡

16. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፈል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0113 383 638 / 0925 586 338/

ኦሮሚያ ስቴት ዩኒቨርሲቲ ሰበታ ካምፓስ