የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን ሱቆችን ለማከራየት ስለፈለገ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በኪራይ ማስተላለፍ ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን ሱቆችን ለማከራየት ስለፈለገ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በኪራይ ማስተላለፍ ይፈልጋል


Addis Zemen (Sep 22, 2026)

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 10

የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን በስሩ ያሉትን ለተለያዩ ፓርኮች ማለትም የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳዳር ኮርፖሬሽን በውስጡ የሚያስተዳድራቸው በኮርዶር ልማት የለሙ ፓርኮች ውስጥ ለቡ ፣መገኛኛ አካባቢ ፣ ሾላ ፣ ሰሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አካባቢ ፣ መካኒሳ ፣ፒያሳ፣ ቤላ ፣ሲቪል ሰርቪስ አካባቢ ፣ሀያ ሁለት አካባቢ ፣ካዛንቺስ ፣ ብሄረጽጌ ፓርክ ውስጥ ያሉ ሱቆች ፣ ጎሮ ሚካኤል እና አራት ኪሎ ፕላዛ ውስጥ የሚገኙ ሱቆችን ለማከራየት ስለፈለገ፣ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በኪራይ ማስተላለፍ ይፈልጋል።

በመሆኑም የተጠቀሱትን መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራጮች ተጋብዘዋል።

1. ተጫራቾች በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ማቅረብ አለበት።

2. ፓርኮቹ ውስጥ ገብቶ ለመስራት ፍቃደኛ የሆነና የተቋማችን ጋር ውል ገብቶ በገበያ ጥናት እና የመነሻ ዋጋ መሰረት ተወዳድረው አስፈላጊውን ክፍያ የሚከፍልና በውሉ መሰረት ግዴታውን መወጣት የሚችል።

3. በግቢ ያሉ ፋውንቴኖችንና ፣ መናፈሻዎችን ፣ የመጸዳጃ ቤቶችን ፣ የጽዳት ፣ የጥበቃ ፣የተለያዩ ጥገናዎችን ከሌሎች ተከራዮች ጋር በመሆኑ ማስጠገን ፣ መቆጣጠርና በአግባቡ ማስተዳደር የሚችል።

4. ለህዝብ የሚሰጡ አገልግሎቶችን ተመጣጣኝ የገበያ ዋጋ ለማቅረብ ፍቃደኛ የሆነ።

5. ኮርፖሬሽኑና የከተማ አስተዳደሩ በሚወጣው የስራ ሰዓት፣ ቅዳሜ እና እሁድ ፣ በዓላትን እንዲሁም ምሽትን ጨምሮ አገልግሎት መስጠት የሚችል።

6. አሸናፊነት ከታወቀ በኃላና ውል ከወሰደ በኃላ በ3 ቀን ውስጥ ስራ መጀመር የሚችል።

7. ስታንዳርዱን የጠበቀ እና የኮሪዶር ልማቱን የሚመጥን እቃዎችን ይዞ መግባት የሚችል።

8. ከተቻለ በሬስቶራንት ፣ በካፌ እና ህዝብ መዝናኛ ፓርክ ላይ ልምድ ያለውና መረጃ ማቅረብ የሚችል

9. ተጫራቾች 50000.00 (ሀምሳ ሺህ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሲፒኦ ወይም ባንክ ጋራንቲ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን ስም ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

10. ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 500 /አምስት መቶ ብር/ መገናኛ ዘፍመሽ ፊት ለፊት ታሜጋዝ ህንጻ ላይ ሶስተኛ ፎቅ የፋይናንስ ዳይሬክትሬት ቢሮ ውስጥ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ አስር ተከታታይ የስራ ቀን ከጠዋት 2፡30 እስከ 11፡3ዐ ሰዓት ድረስ በመቅረብ መግዛት ይቻላል።

11. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ፋይናንሻል ዶክመንት በአንድ ፖስታ እና ቴክኒካል ዶክመንት በአንድ ፖስታ እንዲሁም ሲፒኦ ለብቻው በማሸግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ሳጥኑ እስከሚታሸግበት ከ10ኛው ተከታታይ የስራ ቀን በኃላ ከአለው 11ኛው ቀን ጠዋት 4፡00 ድረስ ለዚህ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።

12. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ሳጥኑ ታሽጎ በዚያው ቀን ጠዋት 4፡30 መገናኛ ዘፍመሽ ፊት ለፊት ታሜጋዝ ህንጻ ላይ ሶስተኛ ፎቅ በግዥና ንብረት ዳይሬክትሬት ቢሮ ውስጥ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ይከፈታል።

13. የጨረታ መክፈቻው ቀን ቅዳሜና እሁድ ላይ የሚውል ከሆነ በቀጣዩ ሰኞ በተጠቀሰው ሰዓት ተዘግቶ የሚከፈት ይሆናል።

14. ዘግይቶ የደረሰ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።

15. ኮርፖሬሽኑ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ፡- ስልክ ቁጥር 0915862636 / 0923389872 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሕዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *