የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ፅ/ቤት በ2019 በጀት አመት የሚያገለግሉ የተለያዩ እቃዎችና አገልግሎቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ፅ/ቤት በ2019 በጀት አመት የሚያገለግሉ የተለያዩ እቃዎችና አገልግሎቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Sep 22, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር አቃ/ፐ/002/2019

የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ፅ/ቤት የ2019 በጀት አመት ሁለተኛ ዙር ግልጽ ጨረታ የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከ/ፐ/ሰ/የሠ/ሀ/ል/ፅ/ቤት የመንግስት ግዥ አስተዳደር ቡድን በስሩ ለሚገኙ የተለያዩ ጽ/ቤት እና ሰራተኞች በ2019 በጀት አመት የሚያገለግሉ የተለያዩ እቃዎችና አገልግሎቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። በመሆኑም መስፈርቱን የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።

  • ሎት 1፡- የተለያዩ ሳይዝ ያላቸው ጊቢ ለማስዋቢያ የሚያገለግሉ አትክልቶች
  • ሎት 2 ፡- የተለያዩ የኤሌክትሪክ እቃዎች
  • ሎት 3 ፡- የእንጨት ውጤቶች
  • ሎት 4 – የተለያዩ የካሜራ ግብአቶች
  • ሎት 5 ፡- የተለያዩ የጽዳት እቃዎች
  • ሎት 6 ፡- የደንብ ልብሶች
  • ሎት 7፡- የቢሮ እድሳት የሚያስፈልጉ ግብዓቶችን በራሱ አቅርቦ አገልግሎት የሚሰጥ
  • ሎት 8፡- ለጽዳት ሰራተኞች እና ለአትክልተኞች ለስራ የሚሆኑ ግብዓቶች

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ።

1. በዘርፉ በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው

2. የዘመኑ ግብር የከፈሉና ለዚህም ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ

3. ቫት ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ

4. የጨረታ ማስከበሪያ በየሎቱ የተመደበውን ሲፒኦ ማቅረብ የሚችሉ

5. የአቅራቢነት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል

የሲፒኦ መጠን

  • ሎት 1፡- 50,000.00 (አምሳ ሺህ ብር)
  • ሎት 2 ፡- 50,000.00 (አምሳ ሺህ ብር)
  • ሎት 3 30,000.00 (ሰላሳ ሺህ ብር)
  • ሎት 4 – 20,000.00 (ሃያ ሺህ ብር)
  • ሎት 5 ፡- 20,000.00 (ሃያ ሺህ ብር)
  • ሎት 6 ፡- 20,000.00 (ሃያ ሺህ ብር)
  • ሎት 7፡- 50,000.00 (አምሳ ሺህ ብር)
  • ሎት 8፡ 20,000.00 (ሃያ ሺህ ብር) (CPO ሲያሰሩ ለአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት ብለ ያሰሩ)

1. ተጫራቾች የማይመለስ 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል እንዲሁም ለጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ማኅበራት በሀገር ውስጥ ምርት የተሰማሩ በአምራችነት ወይም በሻጭ የተሰማሩ እና ካደራጃቸው አካል 6 ወር ያላለፈው የድጋፍ ደብዳቤ በማቅረብ በነፃ መውሰድ የሚችሉ ሲሆን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ የስራ ቀናት አቃ/ቃ/ክ/ከተማ ፐ/ሰ/የሰ/ሀ/ል/ፅ/ቤት የመንግስት ግዥ አስተዳደር ቡድን 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 508 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።

2. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ መሙላት ያለባቸው ቫትን ጨምሮ ያለውን ዋጋ ሲሆን የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናል እና ኮፒ በተለያየ ፖስታ በማድረግ ኦርጅናል ላይ ኦርጅናል ኮፒ ላይ ኮፒ በማለት በማሸግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር ( 10) ተከታታይ የስራ ቀናት አየር ላይ በማዋል በአስራ አንደኛው የስራ ቀን እስከ 4፡00 ሰዓት ብቻ ተጫራቾች ሰነድ በማስገባት 4፡00 ሰዓት ላይ ጨረታው ታሽጎ በዕለቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቢሮ ቁጥር 508 ጨረታው ይከፈታል።

3. ተጨራቾች ናሙና ለሚቀርብባቸው እቃዎች ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል

4. ተጫራቾች በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሰነድ ላይ የድርጅታቸውን አድራሻ ስም፣ ማህተምና ፊርማ ማስፈር ይኖርባቸዋል።

5. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

  • ለተጨማሪ መረጃ፡- አድራሻ፡- ከቃሊቲ መናኽሪያ ፊት ለፊት ባለው የአስተዳደሩ ህንፃ ላይ 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 508 መጠየቅ ይቻላል።
  • የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ፐ/ሰ/የሰ/ሀ/ል/ጽ/ቤት የግዥ አስተዳደር ቡድን

የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ፅ/ቤት