Be'kur (Sep 21, 2026)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጓጉሳ ሽኩዳድ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግ/ን/አስ/ቡድን በ2019 በጀት ዓመት ለጓ/ሽ/ወ/ አስተዳደር ቢሮ ግንባታ
- ሎት 1. የቤት እና የቢሮ እቃ ፣
- ሎት 2. የጓ/ሽ/ወ አስተዳደር ቢሮ አጥር ግንባታ ሙሉ ማቴሪያሉን መስሪያ ቤቱ ችሎ የጉልበት፣
- ሎት 3. የህንፃ መሳሪያ በሎት ጥቅል መግዛት ይፈልጋል፡፡
የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘርፉ ንግድ ፍቃድ ሰርቲፊኬት፣ የንግድ ስራ ፈቃድ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የቲን ተመዝጋቢ ለመሆናቸዉ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የቤት እና የቢሮ እቃ እና የጓ/ሽ/ወ አስተዳደር ቢሮ አጥር ግንባታ የጉልበት የተዘጋጀውን ስፔስፊኬሽን በትክክል በማጥናት በዋጋ ማቅረቢያ ሰነዱ ላይ የአንዱንና ጠቅላላ ዋጋ በትክክል መሞላት አለባቸው፤ ስርዝ ድልዝ ያለበት ዋጋ ማቅረቢያ ተቀባይነት የለውም፡፡
- የአስተዳደር ቢሮ አጥር ግንባታው ተወዳዳሪ ደረጃ 05 እና በላይ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የጓ/ሽ/ወ አስተዳደር ቢሮ አጥር ግንባታ የጉልበት ቴክኒካልና ፋይናንሻል በተለያየ ፖስታ ማስገባት አለባቸው፡፡
- በዋጋው ማቅረቢያ ላይ የተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪል ስም፣ ፊርማና የድርጅቱ አርማ ያለው ማህተም መኖር አለበት፡፡ በተጨማሪ በፖስታው ላይ ያጫራቹን መ/ቤት ስምና የራሳቸው አድራሻ በትክክል ማስቀመጥ አለባቸው፡፡
- በሌላው ዋጋ ተንተርሶ መወዳደር አይፈቀድም፡፡
- የሞሉት ዋጋ ከ500 ሽህ ብር በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ፖስታዎች ላይ የንግድ አድራሻውንና ስሙን በመግለጽ በደንብ በታሸገ ፖስታ በማሸግ የሞላዉን ዋጋ ኦርጅናል ፖስታ የጓ/ሽ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት የግዥ ን/አስ/ ቡድን ባዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ከቀረበዉ ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ የተመሰከረ ሲፒኦ ፣በቢድ ቦንድ ወይም በመሂ 1 በማስያዝ በፖስታዉ ዉስጥ አሽጎ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ ይህ ሳይሆን ቢቀር ከጨረታዉ ይሰረዛል፡፡
- በጨረታው ለተሸነፉ ተወዳዳሪዎች ያስያዙት ገንዘብ የጨረታው አሸናፊ ተለይቶ ውል ከወሰደ በኋላ ይመለስለታል፡፡
- አሸናፊው አሸናፊነቱ ከተገለፀ በኋላ በሚቀጥሉት 5 የስራ ቀናት በኋላ ባሉ 10 ተከታታይ ቀናት ዉስጥ የዉል ማስከበሪያ ካሸነፈዉ ከጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ በባንክ የተመሰከረለት በባንክ የተመሰከረ ሲፒኦ ወይም በመሂ 1 በማስያዝ ዉል መያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- በጨረታ ውድድር ወቅት ቅር የተሰኘ ተጫራች አሸናፊው በተገለጸለት 5 የስራ ቀናት ቅሬታቸውን ማቅረብ ይችላሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ያለ በቂ ምክንያት ውሉን ካፈረሰ ያስያዘውን ገንዘብ በመቀጫ ለመንግስት ገቢ ይሆናል፣ በህግም እንዲጠየቅ ይደረጋል፡፡
- የጨረታው ሳጥን ከታሸገ በኋላ የሚቀርብ ጨረታ ውድድር ጥያቄ ወይም ማስተካከያ ተቀባይነት የለውም ጨረታው ከመታሸጉ በፊት ራሳቸውን ከጨረታው ማግለል ይችላሉ፣ያ ሳይሆን ቢቀር ያስያዙት ገንዘብ አይመለስም፡፡
- ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሀሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታው ራሳችውን ማግለል አይችሉም፡፡
- ጨረታውን ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታው ውጭ እንደሚሆኑ ፣ለወደፊቱ በመንግስት የግዥ ጨረታ እንዳይሳተፉ እንደሚያደርግና ያስያዙት ገንዘብ እንደሚወረስ ማወቅ ይኖርባቸዋል፡፡
- ማንኛውም መስፈርቱን የሚያሟሉ ተጫራቾች ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለቤትና ቢሮ ዕቃዎች እና የህንፃ መሳሪያ 10 ተከታታይ ቀናት በጋዜጣ ታትሞ ይቆይና በ11ኛው ቀን 4፡00 ይዘጋና በዚሁ ቀን 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ይከፈታል፣ የሚከፈትበት ቀን በአል ከሆነ በሚቀጥለው ቀን ይከፈታል፡፡
- መስፈርቱን የሚያሟሉ ተጫራቾች ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአስተዳደር ቢሮ አጥር ግንባታው በጋዜጣ ከታተመበት ቀን ጀምሮ 20 ተከታታይ ቀናት ይቆይና ፤በ21ኛው ቀን 4፡00 ይዘጋና በዚሁ ቀን 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ይከፈታል፣ የሚከፈትበት ቀን በአል ከሆነ በሚቀጥለው ቀን ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ 20በመቶ የመጨመርም ሆነ የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- የጨረታ ሠነዱን ቢሮ ቁጥር 06 በመምጣት 400 ብር በመክፈል መዉሰድ ይችላሉ፡፡
- የማቴሪያል ማስረከቢያ ቦታ ጓ/ሽ/ወ/ ንብረት ክፍል ማስረከብ የሚችል መሆን አለበት፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 058 229 00 50 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የጓ/ሽ/ወ/ ገንዘብ ጽ/ቤት