በኮ/ቀ/ክ/ከተማ አስተዳደር ወረዳ 07 ትም/ጽ/ቤት አዲስ ተስፋ ቅድመ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት የተለያዩ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በኮ/ቀ/ክ/ከተማ አስተዳደር ወረዳ 07 ትም/ጽ/ቤት አዲስ ተስፋ ቅድመ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት የተለያዩ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Sep 24, 2026)

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ መለያ ቁጥር 001/2019

1. በኮ/ቀ/ክ/ከተማ አስተዳደር ወረዳ 07 ትም/ጽ/ቤት አዲስ ተስፋ ቅድመ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

  • ሎት 1 አላቂ የፅህፈት መሳሪያዎችና መገልገያዎች
  • ሎት 2 የደንብ ልብስ
  • ሎት 3 አላቂ የጽዳት መገልገያዎች
  • ሎት 4 የህትመት ውጤቶች
  • ሎት 5 ቋሚ እቃ
  • ሎት 6 የኤሌክትሮኒክስ ጥገና

በዚህ መሰረት በጨረታ መሳተፍ የምትፈልጉ ከዚህ በታች የተጠቀሰውን መስፈርት የሚያሟሉ ድርጅቶችና ግለሰቦች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋበዛሉ፡፡

2. ተጫራቶች የገንዘብ እና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ባወጣው የእቃ ኣቅራቢዎች ዝርዝር እና በገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

ተጫራቾች የ2019 ዓ.ም ግብር የከፈሉና ለ2019 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ፍቃድ መሆኑን የሚገልፅ አግባብነት ያለው ማስረጃ ቫት ሰርተፍኬት ኮፒውን ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

3. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ የስራ ቀናት የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በአዲስ ተስፋ ቅ/አ/አመ ደ/ት/ቤት የግዥ ቢሮ ቁጥር 6 በመቅረብ ከሎት 1 እስከ ሎት 6 ላሉት ለእያንዳዳቸው የማይመለስ ብር 500.00/ አምስት መቶ ብር ብቻ ከፍለው መውሰድ ይኖርበታል፡፡

4. የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚያው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ይከፈታል ይህ ቀን የበአል ቀን ወይም እረፍት ቀን ከሆነ በቀጣይ የስራ ቀን ይከፈታል፡፡

5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ኦርጅናልና ኮፒ በመለየት እና ለየብቻ በማሸግ ከጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት በፊት የጨረታ ማስገቢያ ቦታ በት/ቤቱ ፋይናንስ ግዥ ቢሮ ቁጥር 6 ለጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ቼከ/ሲፒኦ/ ከጨረታው ሰነድ ጋር በፖስታ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

  • ለሎት 01 የጨረታ ማስከበሪያ 20,000.00 (ሀያ ሺ ብር)
  • ለሎት 02 የጨረታ ማስከበሪያ 20,000.00 (ሀያ ሺ ብር)
  • ለሎት 03 የጨረታ ማስከበሪያ 15,000.00 (አስራ አምስት ሺ ብር)
  • ለሎት 04 የጨረታ ማስከበሪያ 10,000.00 (አስር ሺ ብር)
  • ለሎት 05 የጨረታ ማስከበሪያ 15,000.00 (አስራ አምስት ሺ ብር)
  • ለሎት 06 የጨረታ ማስከበሪያ 3000.00 (ሶስት ሺ ብር)

6. ተጫራቾች በሚወዳደሩበት እቃዎች በሙሉ ጨረታው ከመከፈቱ ሁለት ቀን በፊት ከሎት–1 እስከ ሎት 4 ሳምፕልና ናሙና ማቅረብ አለባችሁ ሎት 5 በፎቶ የተደገፈ ያላቀረበ ተጫራች ለውድድር አናቀርብም

7. በግዥ አዋጅ መሰረት ለጥቃቅንና አነስተኛ ልማት ልዩ አስተያየት የሚደረግ ሲሆን በጥቃቅንና አነስተኛ ስለመደራጀታቸው የሚገልፅ ከተደራጁበት ተቋም በፅ/ቤቱ ሀላፊ የተረጋገጠ የዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡

9. የትራንስፖርት አገልግሎት አቅራቢው የት/ቤቱ እስቶር እቃ ግምጃ ቤት ድረስ አምጥቶ የሚያስረክብ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

10. የእቃውን 20 ፐርሰንት መጨመር ወይም መቀነስ መ/ቤቱ የሚችል መሆኑና ጠቅላላ ዋጋ 25 ፐርሰንት ለ6 ወር ድረስ ጨምሮ ሊያዝ የሚችል መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

11. ተጫራቾች በተወዳደሩበት ዋጋ ኣሸናፊነታቸው ከተገለፀላቸው ከ5 እስከ 7 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ቀርበው የቅሬታ ጌዜ ጠብቆ የውል ማስከበሪያ 10 ፐርሰንት ለግዢ ፈፃሚው አካል ማስያዝ አለባቸው ያስያዙትን ገንዘብ ተመላሽ የሚሆነው በውሉ መሰረት የሚጠበቅባቸውን ግዴታ ከተወጡና ውሉን ተመላሽ ሲያደርጉ ነው ተጫራቾች በገዙት ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ መሙያ ቫትን ጨምሮ በግልፅ መሙላት አለባቸው፡፡

12. ት/ቤቱ የተሻለ ዜዴ ወይም አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው

አድራሻ– በኮ/ቀ/ከ/ከተማ ወረዳ 07 ከቤተል ሆስፒታል ወደ ውስጥ ገባ ብሎ ፖሊስ ጣቢያው ጀርባ

ለተጨማሪ መረጃ፡ በስልክ ቁጥር 011–349-94-59 ደውለው ይጠይቁ

አዲስ ተስፋ ቅደመ አ/አ/መካከለኛ ደ/ት/ቤት