በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 2 ስኳር ፋብሪካ በብሄራዊ ግልፅ ጨረታ Safety Material (የአደጋ መከላከያ አልባሳት ግዥ) መግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 2 ስኳር ፋብሪካ በብሄራዊ ግልፅ ጨረታ Safety Material (የአደጋ መከላከያ አልባሳት ግዥ) መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Sep 25, 2026)

Safety Material (የአደጋ መከላከያ አልባሳት ግዥ)

ብሔራዊ የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር፡– አሸጨ/0017ኦኩስፋ-2/2019 ዓ.ም.

  1. በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 2 ስኳር ፋብሪካ በብሄራዊ ግልፅ ጨረታ Safety Material (የአደጋ መከላከያ አልባሳት ግዥ) መግዛት ይፈልጋል፡፡
  2. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ብቁ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ /CPO/ ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የ120 ቀን የባንከ ዋስትና /BID BOND በመስኩ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ሥራ ፍቃድ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ተጫራቾች በመንግስት ግዥ የዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር/supplier List ውስጥ መካተታቸውን የሚያረጋግጥ የምስከር ወረቀት እና በተጨማሪ የበጀት ዓመቱን ታክስ ክሊራንስ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡
  3. ጨረታው በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 (አስራ አምስት) ቀን ውሎ በአስራ ስድስተኛ ቀን ይከፈታል፡፡ የጨረታውን መክፈቻ ትክክለኛ ቀን በጨረታ ሰነዱ ላይ በግልጽ ተቀምጧል፡፡ ዘግይቶ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድ ውድቅ ይደረጋል፡፡
  4. ብቁ ተጫራቾች በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የተሟላ የጨረታ ሰነድ ለሁሉም የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መዝጊያ ቀን ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት (ከሰኞ እስከ ዓርብ ከሰዓት በፊት ከ2፡00-6፡00፣ ከሰዓት በኋላ ከ7፡00-10፡30 እና ቅዳሜ ከሰዓት በፊት ከ2፡00-6፡00) ቀጥሎ በተመለከተው አድራሻ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
  5. የጨረታው ሰነድ የሚሸጥበት ለውድድር የቀረበ ሰነድ የሚገባበትና የሚከፈትበት አድራሻ ቀጥሎ በተጠቀሰው ነው፡– 5.1. አሞ ኩራዝ ቁጥር 2 ስኳር ፋብሪካ የስኳር ፋብሪካዎች ማስተባበሪያ ቢሮ ቶታል ሶስት ቁጥር ማዞሪያ 300 ሜትር ከፍ ብሎ ተዘነኦ ሆስፒታል አጠገብ የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ግቢ ውስጥ፡፡ ስልክ ቁጥር፡ 09-91-14-94-85/0986862766/ 0940209464 አዲስ አበባ/ ኢትዮጵያ
  6. ተጫራቾች ለሁሉም ሎቶች አንድ ላይ የጨረታ የማስከበሪያ ዋስትና ብር 30,000.00 (ሰላሳ ሺህ ብር) በሲፒኦ ወይም በባንክ የተረጋገጠ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  7.  የዕቃው ርክክብ የሚፈፀመው ኦሞ ኩራዝ ቁጥር ሁለት ስኳር ፋብሪካ አዲስ አበባ ማስተባበሪ ቢሮ ነው፡፡
  8. ጨረታው ፀንቶ የሚቆየው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ30 ቀናት ነው፡፡
  9.  የጨረታው ማስከበሪያ ዋስትና ፀንቶ የመቆያ ጊዜ የጨረታው ዋጋ ፀንቶ ከሚቆይበት የመጨረሻ ቀን በኋላ ለ28 ቀናት ነው፡፡
  10. ፋብሪካው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ኦሞ ኩራዝ ቁጥር-2 ስኳር ፋብሪካ

Tel-0940209464

ኃይል ውሃ

አዲስ አበባ ግዥ ማስተባበሪያ ቢሮ

Tel: 09-91-14-94-85/0986862766

አዲስ አበባ

በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ

የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 2 ስኳር ፋብሪካ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *