Addis Zemen (Sep 25, 2026)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 2 ትምህርት ጽ/ቤት የህዝባዊ ሰራዊት ቅድመ አንደኛ አንደኛና መለስተኛ ደረጃ ት/ቤት ለት/ቤቱ አገልግሎት የሚዉሉ የተለያዩ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ተጫራቾች ከዚህ በታች የተገለፁትን መስፈርት የምታሟሉ ሁሉ በጨረታው መሳተፍ ትችላላችሁ፡
- በመስኩ አግባብነት ያለው የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው።
- ዘመኑ ግብር የተከፈለበት ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የተመዘገቡበት ማስረጃ ማቅረብ አለበት።
- የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይነት መረጃ ያላቸው።
- ጥራት ያለው ዕቃ ማቅረብ የሚችሉና ጨረታ ከመከፈቱ በፊት የዕቃዎቹን ናሙና እና በፎቶ አስቀድሞ ማቅረብ የሚችሉ።
- የጨረታ ማስከበሪያ የሚመለስ ብር 10,000.00/ አስር ሺህ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ ቼክ CPO/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ለጨረታ ሰነድ ሽያጭ የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ከግዢ እና ፋይናንስ ክፍል መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ላይ የድርጅቱ ስም ከብ ማህተም እና ፊርማ በታሸገ ኢንቭሎፕ ዉስጥ በማድረግ ማስገባት አለባቸው።
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን አለበት በገዙት ዝርዝር ሰነድ ላይ በግልፅ መፃፍ አለባቸው ስርዝ ድልዝ ካለ ተጫራጩ ፊርማውን ከአጠገቡ ማሰቀመጥ ግዴታ አለበት።
- ጨረታው ለአስር ተከታታይ የስራ ቀናት ክፍት ሆኖ በአስራ አንደኛው ቀን ከቀኑ በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ ወዲያውኑ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት በምክትል ርዕሰ መምህር ቢሮ ይከፈታል።
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ላይ የአንዱን ዋጋ የሞላውን በጠቅላላ ድምር ላይ ማሰቀመጥ ይጠበቅበታል።
- ተጫራቹ ያሸነፈበትን የጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ቼክ/CPO/ ማስያዝ ይጠበቅበታል።
- ት/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ ፡– ፈረንሳይ ለጋሲዮን ከታክሲ ማዞሪያ ከፍ ብሎ የካ ኢንዱስትሪያ ኮሌጅ ፊት ለፊት
የሚገኝው ህዝባዊ ሰራዊት ቅድመ መደበኛና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት
ስ.ቁ 01111400 80 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል
p.o.box 20055
በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 2 ትምህርት ጽ/ቤት የህዝባዊ ሰራዊት ቅድመ አንደኛ አንደኛና መለስተኛ ደረጃ ት/ቤት