Addis Zemen (Sep 25, 2026)
ውስን የጨረታ ማስታወቂያ
በደብረ ብርሃን ዩኒቨርስቲ መገዘዝ ንግድና የማማከር ስራዎች ኢንተርፕራይዝ ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን ዕቃዎች ማለትም፡–
- ሎት 1፡ የእንስሳት መኖ ማቀነባበሪያ ግብዓት
- ሎት 2፡ 45 ቀንና በላይ የሆናቸው የእንቁላል ጣይ ቄብ ዶሮ ግዥ ን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባችኋል።
በዚህም መሠረት፡
- ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩ ሆነው የዘመኑ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፍኬት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ከግብር ሰብሳቢው ባለስልጣን የተሠጠ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ለሎት አንድ ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) እና ለሎት ሁለት ብር 50,000.00 /ሃምሳ ሺህ ብር/ በባንክ በተመሰከረ ሲፒኦ ብቻ በማሰራት ከዋናው የዋጋ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ ቀኑ አስር ሰዓት ድረስ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ደብረ ብርሃን ዩኒቨርስቲ ቅጥር ግቢ ውስጥ ከኢንተርፕራይዙ ቢሮ መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሣባቸውን የያዘ የዋጋ ሰነድ ዋናና ቅጅ ለየብቻው በታሸገ ኢንቨሎኘ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 ቀናት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ በኢንተርፕራይዙ ቢሮ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እንዲሁም ጨረታውን መታዘብ የሚፈልግ ማንኛውም አካል በተገኙበት ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ በወጣ በ10ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ 4፡30 በግልፅ ይከፈታል። የመክፈቻው ቀን በሳምንቱ የዕረፍት ቀናት ወይም በዓል ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተገለፀው ሰዓትና ቦታ በግልፅ ይከፈታል። / ትክክለኛው የመክፈቻ ቀን በጨረታ ሰነዱ ላይ የሚገለፅ ይሆናል።
- ተጫራቾች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተመስርተው የመወዳደሪያ ዋጋ ማቅረብ አይችሉም።
- ኢንተርፕራይዙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥራችን /+251925750633 / 0913497204 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
በደብረ ብርሃን ዩኒቨርስቲ መገዘዝ ንግድና የማማከር ስራዎች ኢንተርፕራይዝ