የቦታው ስፋት 125.95 ካ.ሜ የሆነ የድርጅት ቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ – test3.diretenders.com

የቦታው ስፋት 125.95 ካ.ሜ የሆነ የድርጅት ቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ


Addis Zemen (Sep 25, 2026)

የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

የፍ/ባለመብት ወ/ሮ ጽጌ ገብሩ የህፃን ኑሃሚን ተስፋዬ ሞግዚትና አስተዳዳሪ እና በፍ/ ባለዕዳ እነ ወ/ሮ ድርብነሽ ኃ/ሚካኤል (11 ሰዎች) መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 121970 በ25/9/2018 ዓ.ም እና በኮ/መ/ቁ 18138 በ28/4/2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በአዲስ ከተማ ክ/ ከተማ በቀድሞው ወረዳ 07 በአሁኑ ወረዳ 6 በእነ ወንድሙ ሀይለሚካኤል ስም በካርታ ቁጥር 007/54/1/12669 የተመዘገበ በንጽጽር ጠቅላላ የቦታው ስፋት 125.98 ካ.ሜ የሆነ ቤትና ይዞታ ቦታው ቤቱ/ ቦታው በአካባቢው የውስጥ ለውስጥ መንገድ 3.3 ካ.ሜ የሚነካው ጠቅላላ በፕሮፖርሽን ለግለሰቡ የሚደርሰው የቦታው ስፋት 125.98 ካ.ሜ ቤቱ/ቦታው ድርጅት (ንግድ ቤት) ያለው የሆነው የሐራጅ ሽያጭ መነሻ ዋጋ ብር 5,512,764.08 (አምስት ሚሊዮን አምስት መቶ አስራ ሁለት ሺህ ሰባት መቶ ስልሳ አራት ብር ከ06/100 ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ጥቅምት 16 ቀን 2019 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ በ8፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል። 

የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡3ዐ ጀምሮ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ መጎብኘት የሚችሉ ሲሆን፤ እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን ግምት 1/4ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ C.PO ማስያዝ ይኖርበታል። ከ1/4ኛ አስበልጦም ሆነ አሳንሶ C.RO የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም። በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አ/ጽ/ ቤት ስም CPO አሰርተው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከፈተ አሰርቶ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታው አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳያደርግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታ ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመፃፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን።

የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *