የኢትዮጵያ ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን የደንብ ልብስ (የሥራ እና የአደጋ መከላከያ አልባሳት እና ዕቃዎችን) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የኢትዮጵያ ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን የደንብ ልብስ (የሥራ እና የአደጋ መከላከያ አልባሳት እና ዕቃዎችን) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Sep 25, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ መለያ ቁጥር ኢ.ኢ.ኮ/ብግጨ/05/2019

የኢትዮጵያ ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን የደንብ ልብስ (የሥራ እና የአደጋ መከላከያ አልባሳት እና ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በዚሁ መሠረት ጨረታውን መሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።

1. ተጫራቾች አግባብነት ያለው የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያሳይ የምስክር ወረቀት የሚያቀርቡ ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ በግብር አስገቢው ባለሥልጣን የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እንደዚሁም በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተካተቱ እና መመዝገባቸውን የሚያሳይ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።

2. ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ለእያንዳንዱ ዕቃ ናሙና ማቅረብ አለባቸው።

3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የክፍያ ማዘዣ (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (unconditional Bank Guarantee) አዲስ አበባ ከተማ ከሚገኙ ባንኮች የኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ስም በማሰራት ማቅረብ ይችላሉ። ከኢንሹራንስና ከፋይናንስ ተቋማት ውጪ የሚቀርቡ ዋስትናዎች ተቀባይነት የላቸውም።ስለዚህ የጨረታ ማስከበሪያውን ከቴክኒክ ሰነድ ጋር ማያያዝ አለባቸው።

ሎት

የምድብ ዝርዝር

የተጠየቀው የጨረታ ማስከበሪያ (በኢትዮጵያ ብር)

1

የደንብ ልብስ (የሥራ እና የአደጋ መከላከያ አልባሳት)

70,000

2

አደጋ መከላከያና የመጀመሪያ የህክምና ዕርዳታ ቁሳቁሶች

25,000

4. የጨረታ ሰነዱን የሚፈልጉ ተጫራቾች መረጃ ለማግኘት አጠቃላይ የግዥ አቅርቦትቢሮ ብሎክ አንድ ሁለተኛ ፎቅ የግዥ፣ንብረት እና ፋሲሊቲ ማኔጅመንት ዳይሬክተር  ኢኢኮ ጨረታ ሰነዱን ከዚህ በታች በተቀመጠው አድራሻ በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ ሐሙስ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 6፡30 እና ከሰዓት ከ7፡30 እስከ 10፡00፣ አርብ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 5፡30 እና ከሰዓት ከ7፡30 እስከ 10፡00 በመምጣት መውሰድ ይችላሉ፤

5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን በሁለት የተለያየ ኢንቨሎፖች (ቴክኒካል የመወዳደሪያ ሀሳብ እና ፋይናንሻል የመወዳደሪያ ሀሳብ) ማቅረብ አለባቸው።

6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከታች በተገለፀው ቢሮ በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ።

7. ጨረታው መስከረም 28 ቀን 2019 ዓ.ም. ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ መስከረም 28 ቀን 2019 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ሳጥኑ በሚገኝበት ከዚህ በታች በተገለፀውአድራሻ ይከፈታል።

8. ተጫራቾች የጨረታው አሸናፊ ሆነው ከተመረጡ የውል ማስከበሪያ የአሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% በሲፒኦ ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርበታል።

9. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውን ሙሉ አድራሻቸውን፣ ፊርማቸውን እና ድርጅታቸውን ማህተም ማስፈር አለባቸው።

10. ኮርፖሬሽኑ በማንኛውም ጊዜ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ:-

የኢትዮጵያ ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን ሕንጻ 1፣ ሁለተኛ ፎቅ ፡ በግዥ ንብረትና ፋሲሊት አስተዳደር የጠቅላላ ግዥ አቅርቦት ዲቭዥን ቢሮ ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 05 ከመገናኛ አደባባይ ወደ ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በሚወስደው የቀለበት መንገድ ወደ ኢትዮጵያ ወጣቶችና ስፖርት ማእከል (አደይ አበባ ስታዲየም) በሚያስገባው መገንጠያ መንገድ አጠገብ አዲሱ መሶብ የአንድ ማእከል አገልግሎት የሚሰጥበት ህንጻ.

የኢትዮጵያ ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *