ጣምራ ለማበራዊ ልማት ድርጅት በአዲስ አበባ፣ በኦሮሚያ ክልል እየተገበረ ለሚገኘው ፕሮጀክቶች የሚውል የፍራፍሬ ችግኝ እና የደን ችግኝ አይነቶችን የሚያቀርብ ድርጅቶች ለማወዳደር ይፈልጋል – test3.diretenders.com

ጣምራ ለማበራዊ ልማት ድርጅት በአዲስ አበባ፣ በኦሮሚያ ክልል እየተገበረ ለሚገኘው ፕሮጀክቶች የሚውል የፍራፍሬ ችግኝ እና የደን ችግኝ አይነቶችን የሚያቀርብ ድርጅቶች ለማወዳደር ይፈልጋል


2merkato.com (Sep 25, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ

ጣምራ ለማህበራዊ ልማት ድርጅት ከተመሠረተበት 1990 ዓ.ም ጊዜ ጀምሮ ላለፉት 29 ዓመታት በወጣቶች ልማት፣ በሥነ-ተዋልዶ ጤና፣ በሴቶችና ህጻናት ላይ የሚደርሰውን ጾታዊ ጥቃት በመከላከል፣ በአካባቢ ጥበቃና የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ስርጭትና በሌሎች ማህበራዊ አገልግሎቶች ዙሪያ በኦሮሚያ፣ በደቡብ ክልሎችና በአዲስ አበባ መጠነ ሰፊ እንቅስቃሴ እያደረገ ይገኛል፡፡ ለዚህም ተግባሩ ድርጅታችን ላበረከተው የማኅበረሰብ አቀፍ ጉልህ አስተዋኦ ከሻሸመኔ ከተማ አስተዳደር፣ ከኦሮምያ ክልልና ከኢፊዲሪ መንግስት የሠርትፍኬት፣ የዋንጫ፣ የቦታና የመኪና ሽልማቶችን ያገኘ አንጋፋ ድርጅት ነው፡፡

ድርጅታችን ጣምራ ለማበራዊ ልማት ድርጅት በአዲስ አበባ ፣ በኦሮሚያ ክልል እየተገበረ ለሚገኘው ፕሮጀክቶች የሚውል የፍራፍሬ ችግኝ እና የደን ችግኝ አይነቶችን የሚያቀርብልንን ድርጅቶች ለማወዳደር ጨረታ ያወጣን ሲሆን ዝርዝር የጨረታ ሃሳቡን እና የሚፈለገውን የፍራፍሬ ችግኝ እና የደን ችግኝ  ዝርዝር የያዘውን ዶክመንት የማይመለስ 200 ብር በመክፈል የጨረታ ሰነድ በመግዛት ጨረታውን መሳተፍ የምትችሉ ሲሆን ተጫራች ድርጅቶች ተወካይ መላክ የምትችሉ መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡ 

አድራሻ – ከጃክሮስ ወደ ሳህሊተ ምህረት ቤተክርቲያን በሚወስደው መንገድ አቢሲኒያ ባንክ ጀርባ እንገኛለን

ለበለጠ መረጃ – +251 982024874 / +251 970793680 ይደውሉ፡፡

Deadline – አርብ ፣ መስከረም 22 ቀን 2019 ዓ.ም (Friday, October 2, 2026 , by 6:00 PM)


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *