Addis Zemen (Sep 26, 2026)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የኦሮሚያ መሬት ቢሮ ለመስሪያ ቤቱ የመኪና ዕቃ (Spare part) ከህጋዊ ድርጅቶች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ የሚከተሉትን መሥፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል::
- ድርጅቶች የዘመኑን ግብር የከፈሉና ለተጨማሪ እሴት ታክሰ የተመዘገቡበት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እና ከስቶክ ያለውና ውል ገብቶ በተባለው ጊዜ ውስጥ የመኪና ዕቃ (Spar part) ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN NO/ ያላቸው መሆን አለባቸው፡፡ ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር መግለጫ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ / በመክፈል በኦሮሚያ መሬት ቢሮ 3ኛ ፎቅ ፋይናንስ ክፍል መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ CPO ለመወዳደር ዋጋ 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር ብቻ) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የዕቃዎቹን የዋጋ ዝርዝር በጨረታ ማወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ስማቸውን፣ፊርማቸውንና አድራሻቸውን በማስፈርና ማህተም በማድረግ የጨረታ ዶክመንትኦርጅናልና ኮፒውንየፋይናንሻል ኦርጅናልና ኮፒውንቴክኒከልዶክመንትና CPO በተለያየ በአምስት (5) በታሸገ ኤንቨሎፕ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወይም ባይገኙም ጥቅምት 2/2019 ዓ.ም ከቀኑ በ7፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ8፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
- የጨረታ ሣጥኑ ከታሸገ ወይም ከተከፈተ በኋላ የሚቀርብ ማንኛውም የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
- የጨረታው አሸናፊ አካል በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ ዕቃውን ጨርሶ ማስረከብ የሚችል መሆን አለበት፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በዚህ ስልክ ቁጥር መጠቀም ይችላሉ።
0910 622 700/0919 519 951/0946 653 304/0949 445 72/
አድራሻ፡- ሳርቤት አደባባይን ዞሮ ወደ ቄራ መሄጃ ዋናው አስፋልት 200 ሜትር ላይ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት መስሪያ ቤቶች ቅጥር ግቢ ውስጥ
የኦሮሚያ መሬት ቢሮ