Addis Zemen (Sep 28, 2026)
ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የግዥው መለያ ቁጥር 001/2019
ልደታ ክፍለ ከተማ የወ/ሮ በለጥሻቸው የህዝብ ጤና ጣቢያ የ2019ዓ.ም በጀት ዓመት መግዛት የሚፈልጋቸውን
- ሎት 1፡– የተለያዩ የደንብ ልብስ የጨረታ ማስከበሪያ በብር 4000.00
- ሎት 2፡– የፅህፈት መሳሪያ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 4000.00
- ሎት 3፡– የፅዳት ዕቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 4000.00
- ሎት 4፡– የህትመት ጨረታ ማስከበሪያ በብር 4000.00
- ሉት 5፡– ጥገና የሚደረግላቸው ኮንፒውተር፣ ፕሪንተር፣ የፎቶ ኮፒ ማሽኖችና ሌሎች የጥገና እቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 4000.00
- ሎት 6- ቋሚ የኤሌክትሪክ ዕቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 5000.00
- ሎት 7- ቋሚ የፈርኒቸር ዕቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 5000.00
- ሎት 8፡– የተሸከርካሪ የኪራይ አገልግሎትና የመኪና እና የጄኔሬተር እቃ የጨረታ ማስከበሪርያ ብር 5000.00
- ሎት 9፡– የመድሀኒትና ላብራቶሪ ሪኤጀንቶች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 5000.00
- ሎት 10፡ የተለያዩ ቋሚ አላቂ የካፌ እቃዎች (የሻይ ብርጭቆ፤የቡና ስኒ፣ ረከቦት፣ ትሪ እና የተለያዩ የጨረታ ማስከበሪርያ ብር 5000.00
- ሎት 11፡– የመስተንገዶ አገልግሎት ግዥ የጨረታ ማስከበሪያ በብር 4000.00
- ሎት 12፡– የተለያዩ የደንብ ልብስ ስፌት የጨረታ ማስከበሪያ በብር 4000.00
ብቃት ያላቸው በመስኩ የተሰማሩ ተጫራቾች አወዳድሮ ግዥ/ አገልግሎት መፈፀም ይፈልጋል።
በዚህም መሰረት፣
1. በጨረታው ለመወዳደር ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፍቃድ ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ በመንግስት ግ/ን/አስ/ኤጀንሲ ድህረ ገፅ ላይ በአቅራቢዎች ምዝገባ ዝርዝር የተመዘገቡ የቲንና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒዩ፣ በቁጥር 1 የተገለጹትን በተጫረቱበት ሎት ብዛት ከጨረታው ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
3. ተጫራቾች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት አንስቶ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል በልደታ ክፍለ ከተማ የወ/ሮ በለጥሻቸው የህዝብ ጤና ጣቢያ አዲሱ ህንፃ አንደኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 101 ( ፋይናንስ) ቢሮ በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
4. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን ኦሪጅናልና ኮፒ በታሸገ ኢንቨሎፕ ማስታወቂያ ከወጣበት እለት ጀምሮ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
5. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአስራ አንደኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ ከቀኑ 4፡30 በወ/ሮ በለጥሻቸው የህዝብ ጤና ጣቢያ አዲሱ ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 201 ይከፈታል ፤የመክፈቻ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዐል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ ይከፈታል።
6. ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን እቃዎች ለእያንዳንዱ ከቫት ውጪና ከቫት ጋር ያለውን ዋጋ ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል።
7. የዘገየ ጨረታና በመክፈቻው ላይ ያልተነበበ በፍሉድ የተሰረዘ ጨረታ ተቀባይነት የለውም።
8. ተጫራቾች ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ባሉት ቀናቶች የተወዳደሩበትን ዕቃ ናሙና ማስገባት አለባቸው፤ ናሙና ያልቀረበበት ጨረታ ዋጋ አይኖረውም።
9. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፈባችውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ግዥ ፈፃሚው መስሪያ ቤት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
10. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ለማብራሪያ ጥያቄ፡–
በልደታ ክፍለ ከተማ ጤና ጣቢያ ወ/ሮ በለጥሻቸው የህዝብ ጤና ጣቢያ
የመ/ቤቱ ስልክ 011-854-9237
ልደታ ክፍለ ከተማ የወ/ሮ በለጥሻቸው የህዝብ ጤና ጣቢያ