ሲዳማ ብ/ክ/መ ምስራቃዊ ሲዳማ /ዞን/በ/ወ ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት ለሴክተር መ/ቤቶች አላቂ የጽ/መሳሪያ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

ሲዳማ ብ/ክ/መ ምስራቃዊ ሲዳማ /ዞን/በ/ወ ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት ለሴክተር መ/ቤቶች አላቂ የጽ/መሳሪያ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Sep 28, 2026)

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

ሲዳማ ብ/ክ/መ ምስራቃዊ ሲዳማ /ዞን/በ/ወ ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት ለሴክተር መ/ቤቶች አላቂ የጽ/መሳሪያ እቃዎችን ባቀረቡት በግዥ ፍላጎታቸው መሠረት ሊገዛ ያቀደውን ህጋዊ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በዚህ መሠረት:-

  • በዘረፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ የዘመኑን ግብር የከፈሉና ፍቃድ ያሳደሱ፤
  • የተጨማር እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ፣
  • የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያላቸው፣
  • በአቅራቢዎች ዝርዝር ዉስጥ የተመዘገቡና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
  • በፋይናንስ ህግ መሰረት 3% ዊዝሆልድ መክፈል የሚችሉ፤
  • በተለያየ ምክንያት በዘርፉ ሥራ ላይ ዕገዳ ያልተጣለባቸዉ፤
  • ተጫራቾች የጨረታዉን ማስከበሪያ 15000 (አስራ አምስት ሺህ) ብር በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ማስያዝ የሚችሉ፤
  • ተጫራቾች የጨረታዉ ዋጋ ማቅረብያ ሰነድ የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ) ብር ብቻ በበንሳ ወረዳ ገ/ቅ/ጽ/ቤት ከፍለው መግዛት የሚችሉ፤
  • ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የዕቃ ዋጋ ላይ ቫትን ጨምሮ ያለዉን ዋጋና ከቫት በፊት ያለዉን ዋጋ በግልጽ ማስቀመጥ አለበት፤
  • ተጫራቾች ጨረታዉን ካሸነፉ በኋላ የጨረታ ማስተካከያ መጠየቅ አይችሉም፣
  • ተጫራቾች የጨረታውን ሠነድ ላይ ዕቃ ዋጋ ከሞሉ በኋላ በአንድ ፖስታ ውስጥ ማሸግ ይኖርባቸዋል።
  • ተጫራቾ የሚወዳደሩበት የዕቃ ዋጋ ላይ ቫትን ጨምረዉ ከቫት በፊት ያለው ዋጋ በግለጽ መግለጽ አለባቸው፤
  • ተጫራቾች ጨረታ ካሸነፉ የጨረታ ማስከበሪያ ያሸነፉትን ዋጋ 10 ፐርሰንት በቼክ ወይም በኢፒኦ (CPO) ማስያዝ አለባቸው።
  • መ/ቤቱ እቃው የሚገዛው አይተም በአይተም ነው፤
  • የጨረታ ሰነድ በተጫራቾች መመሪያ መሠረት ተሞልቶ የዋጋ ማቅረቢያ ሰነዱን ኦርጅናሉንና ኮፒውን በሰም በማሸግ በሁሉም ዶኪሜንት ላይ ህጋዊ ማህተም በመምታት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 20 (ሀያ) ተከታታይ በስራ ቀናት ዉስጥ የሚቆይ ሆኖ በ21ኛው ቀን ከጠዋቱ 5፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዕለቱ 5፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ21ኛው ቀን በንሳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በቢሮ ቁጥር 9 ላይ የሚከፈት ሆኖ የተጫራቾች አለመገኘት ግን የጨረታውን ሂደት አያስተጓጉልም።
  • የገበያ ዋጋ ያላገናዘበ ጨረታ ተቀባይነት አይኖረውም።
  • መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፈል የመሰርዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፤
  • የጨረታውን መዝጊያና መክፈቻ ቀን በሥራ ቀን ላይ ካልዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተገለፀው ቦታና ሰዓት ላይ ይሆናል።

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 09 16 01 14 36/ 09 16 36 10 05

የበንሳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *