Addis Zemen (Sep 29, 2026)
1ኛ ዙር ግልጽ የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
በለሚኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 የቦሪ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለቢሮና ለትምህርት አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎች
- የደንብ ልብስ ግዥ ሎት 1
- ለአላቂ የቢሮ እቃዎች ሎት 2
- ለአላቂ የት/ት እቃዎች ሎት 3
- አላቂ የጽዳት እና ሌሎች ዕቃዎች ሎት 4
- ቋሚ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ግዥ ሎት 5
- ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች ሎት 6 በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተወዳዳሪዎች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል።
1. የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸውን ዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ የሚያቀርብ።
2. የገቢዎች እና ጉምሩክ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት።
3. ተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት /ቫት/ የተመዘገቡበትን የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
4. የአቅራቢዎች ምዝገባ ዝርዝር መያያዝ የሚችሉ መሆን አለበት።
5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ በእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ 300 ብር /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት በለሚኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ቦሪ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ሰነዱን መግዛት ይቻላሉ።
6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ የሚኖርባቸው ሲሆን ይኸውም ሎት /የደንብ ልብስ ግዥ 30,000፣ ሎት 2 /ለአላቂ የቢሮ ዕቃዎች 20,000፣ ሎት 3 /ለአላቂ የት/ት ዕቃዎች 20,000፣ ሎት 4/አላቂ የፅዳት እና ሌሎች ዕቃዎች 20,000፣ ሎት 5 ቋሚ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ግዥ 50000፣ ሎት 6 ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች 20,000 በባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ አለበት።
7. የመወዳደሪያ ዋጋው ከነቫት በማስቀመጥ በግልጽ ተጠቅሶ መጻፍ ይኖርበታል።
8. የጨረታው ተሳታፊዎች የሚያቀርቡትን የጨረታ ሰነድ ፋይናንሽያል እና ቴክኒካል ዋናውንና ኮፒ በፖስታ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። በተጨማሪም የሚወዳደሩበት ዕቃ ናሙና /specification/ ማቅረብ አለባቸው።
9. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸው ከታወቀ በኋላ በ15 ቀናት ውስጥ ከት/ቤቱ ጋር ውል መዋዋል አለበት።
10.ተጫራቾች ያሸነፉበትን ደረጃውን የጠበቀ ዕቃዎችን ትዕዛዙ በደረሳቸው በአምስት የስራ ቀናት ውስጥ በናሙናው መሰረት አጠናቀው ለት/ቤቱ ንብረት ክፍል ሲያስረክቡና በጥራት ኮሜቴተፈትሾ ሲያልፍና በተቋሙ ኃላፊ ገቢ እንዲሆን ከታዘዘ በኋላ ይከፍላቸዋል።
11. የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ክፍት ሆኖ በ11ኛው የሥራ ቀን ጠዋት 4፡00 ሰዓት የጨረታው ሳጥን ይታሸግና በዛው ዕለት በ4፡30 ሰዓት ቦሪ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ፋ/ግ/ንብ/አሥ/የቡድን መሪ ቢሮ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
12. የጨረታው አሸናፊ የጨረታው ውጤት ሲታወቅ የውል ማስከበሪያ ካሸነፈበት ጠቅላላ የጨረታ ዋጋ 10% በጥሬ ገንዘብ CPO በቅድሚያ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
13.መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
14. ሁሉም ተጫራቾች ከጥር 1 ቀን ጀምሮ ገቢዎች እና ጉምሩክ ባለሥልጣን ባወጣው መመሪያ መሰረት ካሽ ሬጅስተር ያለው ወይም QR ኮድ ያለው ደረሰኝ ማቅረብ አለባቸው።
አድራሻ፡- ከአያት አደባባይ ወደ ጣፎ በሚወስደው መንገድ በግራ በኩል በመናፈሻ ፊትለፊት 300 ሜትር ገባ ብሎ ይገኛል።
በለሚኩራ ክ/ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት ቦሪ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት