በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 04 ጨፌ ጤና ጣቢያ ደንብ ልብስ፣ አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ አላቂ የጽዳት እቃዎች፣ ህትመት ስራዎች፣ ቋሚ የአይቲ የኤሌክትሮኒስ እቃዎች እና ፈርኒቸር፣ የደንብ ልብስ ስፌት መግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 04 ጨፌ ጤና ጣቢያ ደንብ ልብስ፣ አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ አላቂ የጽዳት እቃዎች፣ ህትመት ስራዎች፣ ቋሚ የአይቲ የኤሌክትሮኒስ እቃዎች እና ፈርኒቸር፣ የደንብ ልብስ ስፌት መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Sep 28, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ

የግዥ መለያ ቁጥር ለሚ ኩ/ክ/ከ/ ጨፌ ጤጣ/ 18/01/2019 ዓ.ም

የጨረታ ቁጥር 01/2019

በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 04 ጨፌ ጤና ጣቢያ የሚገዛው ዕቃ ተዛማጅ አገልግሎት፣

  • ሎት 1 ደንብ ልብስ
  • ሎት 2 አላቂ የቢሮ እቃዎች
  • ሎት 3 አላቂ የጽዳት እቃዎች
  •  ሎት 4 ህትመት ስራዎች
  • ሎት 5 ቋሚ የአይቲ የኤሌክትሮኒስ እቃዎች እና ፈርኒቸር
  • ሎት 6 የደንብ ልብስ ስፌት

ከዚህ በላይ የተገለጸውን ስራ ላይ መወዳደር የምትፈልጉ አቅራቢዎች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል።

1. የዘመኑን ግብር የከፈሉና ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያሳደሱ ተጨማሪ እሴት ታክስ/የቫት ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው ማስረጃ የሚያቀርቡ።

2. ተጫራቾች የጨረታውን ሠነድ የማይመለስ በየሎቱ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር ከፍለው ሠነዱን መውሰድ ይችላሉ።

3. የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተመሰከረለት ሲፒኦ በስተመጨረሻ ተመላሽ የሚሆን ከዚህ በላይ ለተገለጹት ሎቶች ለሚወዳደሩበት ሎት በመለየት/ ለሎት 1. 10,000.00 /አስር ሺህ ብር/ ለሎት 2. 5,000.00/ አምስት ሺህ/ ብር ለሎት 3 10,000.00 /አስር ሺህ/ ብር ለሎት 4- 5.000.00/አምስት ሺህ ብር ለሎት 5 10,000.00 /አስር ሺህ ብር/ ሎት 6 5,000.00 አምስት ሺህ ብር/ ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን በመለየት ፖስተው ላይ በመግለጽ ዋናውን ፎቶ ኮፒ በማድረግ የገዙትን ዋናውን የጨረታ ሰነድ እና ፎቶ ኮፒውን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በጤና ጣቢያው ግዥ ክፍል በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

4. በጥቃቅን እና አናስተኛ ለተደራጁ ማህበራት ካደራጃቸው አካል ለሚያመርቱበት ስራዎች ከባላይ ሃላፊ ተፈርሞ ለጨረታ ማስከበሪያ እና ለውል ማስረከቢያ ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

5. ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ተዘግቶ በዚያው ቀን 5፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጤና ጣቢያው ባዘጋጀው ቢሮ ይከፈታል።

6. በጨረታው አሸናፊ የሆኑትን ላሸነፉበት የውል ማስከበሪያ 10% በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ቼክ ማቅረብ አለባቸው።

7. የተሰረዘ፣ የተደለዘና ግልጽነት የሌለው የጨረታ ሠነድ ይሰረዛል።

8. ጤና ጣቢያው መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

9. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ዋጋ ስትሞሉ ከነቫት ጨምራችሁ መሙላት አለባችሁ 

አድራሻ:- በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ ዐ4 ጨፌ ጤና ጣቢያ ከውሀ ታንከር ትንሽ አለፍ ብሎ ባለው ማዞሪያ ላይ በመውረድ ወደ ውስጥ አስፓልቱን 200 ሜ ገባ ብሎ የመጨረሻው አርባ ስልሳ ፊት ለፊት እንገኛለን።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 09 04 95 58 01/ 09 20 90 96 26 / 09 17 70 58 11/ ደውለው ማረጋገጥ ይችላሉ።

በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 04 ጨፌ ጤና ጣቢያ