በልደታ ክፍለ ከተማ የወ/ሮ በለጥሻቸው የህዝብ ጤና ጣቢያ የጥገና ስራዎች በጨረታ መሳተፍ ለሚፈልጉ ተቋራጮችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በልደታ ክፍለ ከተማ የወ/ሮ በለጥሻቸው የህዝብ ጤና ጣቢያ የጥገና ስራዎች በጨረታ መሳተፍ ለሚፈልጉ ተቋራጮችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል


Addis Zemen (Sep 28, 2026)

የግንባታ (የእድሳት) ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 001/2019

በልደታ ክፍለ ከተማ የወ/ሮ በለጥሻቸው የህዝብ ጤና ጣቢያ የጥገና ስራዎች በጨረታ መሳተፍ ለሚፈልጉ ተቋራጮችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።

በመሆኑም ለስራው አስፈላጊ የሆኑ ግብአቶችን፣ የተሟላ የሰው ሀይል እና ማሽነሪዎች በማቅረብ በተጠቀሰው ቀናት ውስጥ ስራውን ማጠናቀቅ የሚችል እና የሚቀጥሉትን መስፈርቶች በማሟላት የጨረታ ሰነዱን በአካል በመምጣት ብቻ መውሰድ ይችላሉ።

ሎት

 

የስራው ዓይነት

 

የግንባታ ጊዜ (በቀን)

 

የጨረታ አየር ላይ የሚቆይበት ቀን

ደረጃ

 

የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና መጠን

የጨረታ ሰነድ የሚገባበት ቀን

የጨረታ መክፈቻ ቀን

 

1

– የሻይ ቤት እድሳት፤ የጥበቃ ማማ እድሳት፤ የማይካ ስራ()፡የዴኬር ክፍል ፊትለፊት ያለውን ግሪል ህጻናቶቹ እንዳይወድቁ መሸፈን

 

45 ቀን

 

ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀም ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት

BC7 እና ከዚያ በላይ

 

50,000 ብር በባንክ ትእዛዝ (CPO) ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና

 

ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት 16ኛው ቀን ጠዋት ከ3፡00 እስከ 4፡00 ሰዓት

 

ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት በወጣበት በ16ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ ከቀኑ 4፡30 በወ/ሮ በለጥሻቸው የህዝብ ጤና ጣቢያ አዲሱ ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 201 ይከፈታል

1. ለስራው ህጋዊ ፈቃድ ኖሯቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤ የ2018 ዓ.ም የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው የ2017 ዓ.ም ንግድ ፍቃድ ኖሯቸው ግዴታቸውን እየተወጡ መሆናቸውን የሚገልጽ እና በ2019 በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል ክሊራንስ ከሚመለከተው አካል የሚያቀርቡ ሆነው ጨረታውን አሸናፊ ከሆኑ ግን የታደሰ የንግድ ፈቃድ ውል ከማሰራቸው በፊት ማቅረብ የሚችሉ፣ የ2019 ፈቃድ ያደሱም ቢሆኑም ሁሉም ተጫራቾች ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ፣ ከፌደራል ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚ/ር የምዝገባ ምስክር ወረቀት እና ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለ2019 በጀት ዓመት የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው ከሁለቱም/፣ የአቅራቢነት ምዝገባ ያላቸው (supplier list)፣ ቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው። በልደታ ክፍለ ከተማ በወ/ሮ በለጥሻቸው የህዝብ ጤና ጣቢያ አፈፃፀም ከ 75% በላይ መሆኑን የሚገልፅና መልካም አፈፃፀም (Good Performance) ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ ሆኖ ሁሉም ተወዳዳሪ ተቋራጮች ቀድሞ ለሰሩት ፕሮጀክት ከሰሩበት ተቋም የቅርብ ጊዜ የመልካም የስራ አፈፃፀም ማቅርብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።

2. ተጫራቾች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በስራ ሰአት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 10፡30 ድረስ በልደታ ክፍለ ከተማ በወ/ሮ በለጥሻቸው የህዝብ ጤና ጣቢያ አዲሱ ህንጻ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 101 ከላይ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ዋናው (Original)፤ የማይመለስ ቅጂ (copy) የማይመለስ ብር 200 ብቻ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።

3. ተጫራቾች የወሰዱትን የጨረታ ሰነድ በጨረታው የቴክኒካል ሰነድ ከክፍል አንድ እስከ ሦስት ባለው መሰረት ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት በልደታ ክፍለ ከተማ በወ/ሮ በለጥሻቸው የህዝብ ጤና ጣቢያ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ከላይ በተጠቀሰው ቀን እና ሰአት ብቻ ማስገባት ይኖርባችዋል።

4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (BID BOND or BID SECURITY) በባንክ ትእዛዝ (CPO) ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና /UNCONDITIONAL BANK GUARANTEE/ ከላይ በተጠቀሰው የብር መጠን በልደታ ክፍለ ከተማ በወ/ሮ በለጥሻቸው የህዝብ ጤና ጣቢያ ስም ማስያዝ አለባቸው።

5. ተጫራቾች የወሰዱትን የጨረታ ሰነድን በጨረታው ሰነድ በተቀመጠው መመሪያ መሰረት የመጫረቻ ሰነድ በማዘጋጀት፡-

6. ውድድሩ ቴክኒካል እና ፋይናንሺያል ስለሚኖረው ቴክኒካል አንድ ኦርጂናል እና ቴክንካል ሁለት ኮፒ እና ፋይናንሺያል አንድ ኦርጂናል እና ፋይናንሽያል ሁለት ኮፒ በማሸግ በድምሩ ስድስት ሰነድ ለየብቻ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናም (BID BOND or BID SECURITY) ለብቻ በታሸገ ፖስታ ላይ ፊርማ እና ማህተም በማድረግ ማስገባት ይኖርባችኋል። በተጨማሪም የታሸገውን 6 ፖስታ የፋይናንሻል ሰነድ ሶስቱን ፖስታ በአንድ ፖስታ በማሸግ እና ቴክኒካል ሰነድ ሶስቱን ፖስታ በአንድ ፖስታ በማሸግ ሁለቱን ፖስታና የCPO ፖስታውን በአንድ እናት ፖስታ በማሸግ የድርጅቱን ማህተም እና የሚወዳደሩበትን የስራ አይነት ስም በመጻፍ ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል። ከላይ በተጠቀሰው ቀን እና ሰአት በልደታ ክፍለ ከተማ በወ/ሮ በለጥሻቸው የህዝብ ጤና ጣቢያ ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ የጨረታ ሰነዶችን ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው ከላይ በተጠቀሰው ቀን እና ሰአት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት (ሙሉ በሙሉ ባይገኙ የሚከፈት ይሆናል)።

7. አሰሪው መ/ቤት አሸናፊው ካሸነፈበት አጠቃላይ ስራ 20% መጨመርም ሆነ መቀነስ ይችላል።

8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከማስገባታቸው በፊት የተጫራቾች መመሪያን እንዲያነቡ እና የግንባታ ሳይቱን ማየት ይመከራል።

9. የትኛውንም ከላይ የተዘረዘሩትን ሆነ በጨረታው ሰነድ ላይ የተጠቀሱትን የጨረታ መመሪያ እና ህጎች አለማክበር፣ በሚያስገቡት የመጫረቻ ሰነዶች በሁሉም ገፆች ላይ ማህተም እና ፊርማ አለማድረግ በዋጋ ላይ ያልተፈረመበት ስርዝ ድልዝ (unsigned Rate Correction) እና በዋጋ ላይ ፍሉድ መጠቀም (to use fluid for Rate Correction) ከተወዳዳሪነት ያሰርዛል። በተጨማሪም በስራ ዝርዝር በሙሉም ሆነ በአንድ የስራ አይተም ላይ ዋጋ አለመሙላት (unfilled rate) ከተገኘ ስራውን በነጻ እንደሚሰራ ይወሰዳል።

10. ተጫራቾች የሚያቀርቧቸው የድርጅቱ የስራ ልምድ እና ማንኛውም በቴክኒካል የተጠየቁ ዶክመንቶችን አሰሪ መስሪያ ቤት ኦሪጅናል ዶክመንት የመጠየቅ እና ዶከመንቶቹን ከሰጠው አካል የማጣራት መብቱ የተጠበቀ ነው።

11. የበለጠ ማብራሪያ ካስፈለገ ወ/ሮ በለጥሻቸው የህዝብ ጤና ጣቢያ አዲሱ ህንፃ 2 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 201 ግዥ ከፍል በአካል በመቅረብ መረዳት ይቻላል።

12. አድራሻ፡- ልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ወደ አብነት የሚወስደው መንገድ ተስፋ ኮከብ ት/ቤት ፊት ለፊት ዋናውን አስፓልት ተሻግሮ 100 ሜትር ገባ ብሎ ወ/ሮ በለጥሻቸው የህዝብ ጤና ጣቢያ

መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የመ/ቤቱ ስልክ 011-854-9237
በልደታ ክፍለ ከተማ የወ/ሮ በለጥሻቸው የህዝብ ጤና ጣቢያ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *