Addis Zemen (Sep 29, 2026)
ለመጀመሪያ ግዜ የወጣ የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ብ.ግ.ጨ 001/19
በአራዳ ክፍለ–ከተማ ወረዳ 04 ት/ፅ/ቤት የወ/ሮ ቀለመወርቅ ጥሩነህ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የጽህፈት መሳሪያዎች፣ የህትመት ዕቃ፣የፅዳት ዕቃዎች፣ የጥገና ዕቃዎች፣ የደንብ ልብስ፣ የትምህርት ዕቃ፣ የጥገና ስራዎች እንደ ኮፒውተር፣ ፕሪንተር ፎቶ ኮፒ ማሽን፣ ማባዣ ማሽን ጥገናዎች እንዲሁም ቋሚ ዕቃዎችን ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም እያንዳንዱ አቅራቢ ተጫራች የሚከተሉትን ነጥቦች በገንዘብ የጨረታ ሰነዱን መስሪያ ቤታችን በግንባር በመቅረብ መግዛትና መወዳደር ይችላል።
1. ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን አግባብነት ያለው የታደሰ የንግድ ፍቃድ፣ በመንግስት ግዢ ዕቃ አቅራቢነት የተመዘገቡበትን የምስክር ወረቀትና የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ እና ሌሎች አስፈላጊ መረጃዎችን ከጨረታው ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
2. የጨረታ ሰነዱ በሁለት ፖስታዎች ዋና/Original/ እና ቅጂ/Copy / ኤንቨሎፕ ታሽጎ በጨረታ ሣጥን ውስጥ የጨረታው ማስረከቢያ ሰዓት ከመድረሱ በፊት በወ/ሮ ቀለመወርቅ ጥሩነህ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ፋይናንስ ክፍል መግባት ይኖርበታል።
3. ተጫራቾች ናሙና ለማይቀርብባቸው ዕቃዎች አጭር መግለጫ Specification/ ማቅረብ አለባቸው።
4. እያንዳንዱ ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ /Bid bond/ እያንዳንዱ ጨረታ ላይ በየሎቱ ብር 2,500/ ሁለት ሺህ አምስት መቶ ብር/ በCPO ከዋናው (original) የጨረታ ሠነድ ውስጥ አድርጎ ማቅረብ ይኖርበታል።
5. ተወዳዳሪዎች ለጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ ይህ ጨረታ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 /አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት መስሪያ ቤታችን በግንባር በመገኘት የማይመለስ 200.00/ ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ።
6. የጨረታ ሰነዱ ጨረታው አየር ላይ በዋለ በ11ኛው የስራ ቀን በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል።
7. የጨረታ ሠነድ መቀበያ ሰዓት ከተዘጋ በኋላ የሚቀርብ የመጫረቻ ሠነድ ተቀባይነት አይኖረውም።
8. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡– አዲስ አባባ አራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 04 ከፒያሳ ወደ አዲሱ ገበያ መንገድ ሾላ ከኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ከፍ ብሎ
ስልክ:- 011 126 3242 / 011 155 4573
በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 04 ት/ፅ/ቤት የወ/ሮ ቀለመወርቅ ጥሩነህ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት