በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በምዕራብ አርሲ ዞን አዳባ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የተለያዩ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በምዕራብ አርሲ ዞን አዳባ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የተለያዩ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Sep 29, 2026)

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በምዕራብ አርሲ ዞን አዳባ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በስሩ ላሉት ለተለያዩ መንግስት መስሪያ ቤቶች ከዚህ በታች የተዘረዘሩ የተለያዩ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

እነሱም፦

1. የፅህፈት መሳሪያዎች

2. ቋሚ አላቂ ዕቃዎች እና የፅዳት ዕቃዎች

3. የኤሌክትሮኒክስ እና ፈርኒቸር ዕቃዎች

4. የደንብ ልብሶችን

ከዚህ በታች የቀረበውን መስፈርት የምታሟሉ አቅራቢዎች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።

አስፈላጊ መስፈርቶች

1. ተጫራቾቹ ከሚጫረቱበት ዕቃ ጋር ቀጥታ ግንኙነት ያለውና ዕቃዎቹን በጥራት ለማቅረብ የሚያስችል ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያለውና የዘመኑን ግብር የከፈለ፣VAT ተመዝጋቢነት እና TIN No. እንዲሁም የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል።

2. የጨረታ ማስከበሪያ ተመላሽ የሚሆን በተ.ቁ 1.2.3. እና 4 (ሁሉም ላይ) ከተወዳደሩ 30,000.00 (ሰላሳ ሺህ ብር) እንዲሁም በተ.ቁ 3 እና 4 ላይ ለየብቻ ከተወዳደሩ 20,000 (ሃያ ሺህ ብር) በcpo ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርበታል።

3. ይህ ጨረታ አየር ለይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ 15 (አስራ አምስት) የስራ ቀናት ውስጥ 19/01/2019 ዓ.ም የጨረታ ሰነዱን በማይመለስ ብር 1000 (አንድ ሺህ) ብር ከፍሎ መግዛት ይችላሉ።

4. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሳባቸው ላይ መ/ቤታችን በሰጣቸው የጨረታ ሰነድ ላይ የአንዱ ዋጋ የሚለው ቦታ ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ ያካተተ ዋጋ ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው በመሙላትና የድርጅታቸውን ማህተም፤ ፊርማና ሙሉ አድራሻቸውን በመግለፅ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ አንድ ኦርጅናልና አንድ ፎቶ ኮፒ በሥራ ሰዓት እስከ ቀን 09/ 02 /2019 ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በአንድ ጥቅል ፖስታ በማሸግ አዳባ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ ቤት ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።

5. ጨረታው የሚከፈተው ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ውክልና ያላቸው ሰዎች ባሉት ይሆናል።

6. ከ100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ) በላይ ያሸነፈ ተጫራች የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆን አለበት።

7. ጨረታ የሚከፈተው ከዚህ በላይ የተጠቀሰውን ቀናቶች አልቆ በቀን 10/02/2019 ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ይከፈታል።

8. የሚቀርቡት ዕቃዎች ጥራት ያላቸውና በተሰጠው ስፔስፊኬሽን መሰረት ተሟልተው መቅረብ ይኖርባቸዋል።

9. የዕቃው አቅርቦት ቦታ አዳባ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ሲሆን ማስጫኛና ማውረጃን ጨምሮ ይሆናል።

10. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አመራጭ ከገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

11. ለተጨማሪ መረጃ፡- 022 -663-0255/ 09 13-15 09 29/ 09 15-81 08 37 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

ምዕራብ አርሲ ዞን አዳባ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት