አራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 09 ባሻ ወልዴ ችሎት ጤና ጣቢያ በ2019 የበጀት አመት የተለያዩ ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

አራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 09 ባሻ ወልዴ ችሎት ጤና ጣቢያ በ2019 የበጀት አመት የተለያዩ ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Sep 29, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ

ግልጽ ጨረታ መለያ ቁጥር 01/2019 ዓ.ም

አራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 09 ባሻ ወልዴ ችሎት ጤና ጣቢያ በ 2019 የበጀት አመት የሚያስፈልገውን ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

  • ሎት 1፡– የፅህፈት ማሳሪያዎች እና ህትመት
  • ሎት 2፡– የፅዳት እቃዎች፣ የደንብ ልብስ እና የባለሙያ ደንብ ልብስ ስፌት(ማሰፍያ)
  • ሎት 3፡– ቋሚና አላቂ ዕቃዎች
  • ሎት4፡ የሚወገዱ መዳህኒቶች እና የላብራቶሪ ሪኤጀንቶች
  • ሎት 4:- የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፤ ላፕቶፕ እና ኮምፒውተር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ በጨረታ ላይ ለመካፈል የምትፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን ሁኔታዎች በቅድሚያ መሟላት ይኖርባቸዋል።

1. ተጫራቾች በተሠማሩበት የሥራ መስክ የንግድ ፈቃድና የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸውና የታደሰ የንግድ ፍቃድ ማስረጃ ማቅረብ።

2. ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የእቃ አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ለመሆናቸው የሚያረጋግጥ የምዝገባ ሰርተፍኬት ፎቶ ኮፒ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

3. ተጫራቾች የግብር ክፍያ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው ለሚወዳደሩባቸው እቃዎች የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ መሆናችሁን የሚያረጋግጥ ህጋዊ ማሰረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

4. ተጫራቾች በጨረታ ያሸነፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ወደ መ/ቤታችን ግቢ ማድረስ ይኖረባቸዋል። ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚያገለግል የመጫረቻ ዋጋ 2% በድርጅቱ ስም ሲፒኦ በመዘጋጀት ማረጋገጫውን ከመወዳደሪያ ሠነዶቻቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

5. ተጫራቾች በአንድ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችሉም።

6. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት የጨረታ ሰነድ ላይ በጥንቃቄ ሞልተው በመፈረምና የድርጅቱን ማህተም በማድረግ ዋና እና ኮፒውን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10/አሥር/ የሥራ ቀናት ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

7. መ/ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ ዋጋ ሞልቶ እና የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም አድርጐ የማያቀርብ ተጫራች ተቀባይነት አይኖረውም።

8. የጨረታው አሸናፊ ማሸነፋቸውን በጽሁፍ የምንገልጽላቸው ሲሆን ለጨረታ አፈጻጸም ማስከበሪያ ላሸነፉበት እቃ ዋጋ 10% በማስያዝና ውል በመዋዋል የተመረጡትን እቃዎች በሙሉ በውሉ መሠረት ካላቀረቡ በግዥ ህጉ መሠረት መ/ቤቱ ተጠያቂ ያደርጋል።

9. በጨረታው ያላሸነፉት ድርጅቶች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል።

10. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የማወዳደሪያ ሀሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ እንዲሁም ከጨረታው እራሳቸውን ማግለል እንደማይችሉ ማወቅ አለባቸው።

11. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የያዘ የማይመለስ ብር 200/ ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10/አስር/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ጤና ጣቢያው ቀርበው መውሰድ ይችላሉ።

12. የጨረታው ሳጥን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚሁ አለት ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት ላይ የሚከፈት ሲሆን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት በአራዳ ክ/ከተማ የባሻ ወልዴ ችሎት ጤና ጣቢያ አዳራሽ በግልጽ ይከፈታል።

13. ተጫራቾች ለሚጫረቱባቸው እቃዎች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት የካታሎግ ናሙና ማቅረብ አለባቸው፤ ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ናሙና ማቅረብ አይቻልም፤ ናሙና ያላቀረበ ተጫራች ከውድድር ውጪ ይሆናል።

14. ተጫራቾች ለሚያቀርቧቸው እቃዎች በሙሉ ኦርጅናል ሆኖ ለዚህም ዋስትና ማቅረብ አለባቸው፤ መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ከተገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ ማብራሪያ፡–

አድራሻ፡– ከቱርስት ሆቴል ወረድ ብሎ ልቀት ኮሌጅ ፊት ለፊት

ስልክ ቁጥር 09 73 78 80 50 / 09 73 78 40 00

በአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የባሻ ወልዴ ችሎት ጤና ጣቢያ

አራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 09 ባሻ ወልዴ ችሎት ጤና ጣቢያ