ዘመን ኮንስትራክሸን ኮርፖሬሽን እየገነባቸው ላሉት ለተለያዩ ፕሮጀክቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ስራዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

ዘመን ኮንስትራክሸን ኮርፖሬሽን እየገነባቸው ላሉት ለተለያዩ ፕሮጀክቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ስራዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Sep 28, 2026)

የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

ጨረታ ቁጥር 07/2019፣08/2019:09/2019 እና 1/2019

ዘመን ኮንስትራክሸን ኮርፖሬሽን እየገነባቸው ላሉት

  1. ለተለያዩ ፕሮጀክቶች አገልግሎት የሚውሉ የዳታ ቴሌ፣ ቲቪ፣ ኦዲዮ፣ ፋየሲስተም፣ መብረቅ መከላከያ፣ ኬብል ትሪ እና ሌሎች አቅርቦት እና ገጠማ ስራ ጨረታ ቁጥር 07/2019

2. ለተለያዩ ፕሮጀክቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ኤሌክትሮ መካኒካል (AC System)፣ የባዝ ወይ (BUS WAY Systems) እና ትራፊክ ባርየር (Traffic Barriers) አቅርቦት እና ገጠማ ስራ ጨረታ ቁጥር 08/2019

3. ለተለያዩ ፕሮጀክቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ጀነሬተሮች አቅርቦት እና ገጠማ ስራ ጨረታ ቁጥር 09/2019

4. ለተለያዩ ፕሮጀክቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ሊፍት አሳንሰር አቅርቦት እና ገጠማ ስራ ጨረታ ቁጥር 11/2019 ግዥ ለመፈጸም ህጋዊና ብቃት ያላቸው ፋብሪካዎችና አቅራቢዎች በግልፅ ጨረታአወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን እየገለጽን፤

1. በዘርፉ ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድና፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (T) እና የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስከር ወረቀት ያለው ያላት።

2. የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን ቫትን ጨምሮ 2% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርበታል።

3. የጨረታ ሰነዱን ባ/ዳር ከተማ ዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ቀበሌ 11 እና አ አበባ ለገሃር አመልድ ህንፃ በሚገኘው ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ቢሮ 7ኛ ፎቅ ለተጠቀሱት ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት መውሰድ ይችላሉ።

4. የጨረታ መዝጊያ እና መክፈቻ ቀናት ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለጨረታ ቁጥር 07/2019 እና 08/2019 ኦርጅናልና ኮፒውን እንዲሁም ለጨረታ ቁጥር 09/2019 እና 11/2019 ቴክኒካል እና ፋይናንሺያል ሰነዶች ኦርጅናልና ኮፒውን በመለየት በተለያዩ ፖስታዎች በጥንቃቄ በማሸግ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለጨረታ ቁጥር 07/2019 እና 08/2019 እስከ 15ኛው ቀን (15 ተከታታይ ቀናትን በመቁጠር) እንዲሁም ለጨረታ ቁጥር 09/2019 እና 11/2019 እስከ 20ኛው ቀን (20 ተከታታይ ቀናትን በመቁጠር) ባህር ዳር ዋናው ቢሮ ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 108 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

የጨረታ ሳጥኑ ለጨረታ ቁጥር 07/2019 እና 08/2019 በ15ኛው ቀን እና ለጨረታ ቁጥር 09/2019 እና 11/2019 በ20ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ታሽጎ 8፡30 ይከፈታል። የተጠቀሱት የመክፈቻ እና የመዝጊያ ቀናቶች የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን እስከ ቀኑ 8፡00 ሠዓት ድረስ ማስገባት የሚችሉ ሲሆን በእለቱ ቀን 8፡00 ሰዓት ሳጥኑ ታሽጎ 8፡30 ይከፈታል።

5. የጨረታው ውድድሩ በሎት /በምድብ ድምር ዋጋ የሚታይ ሲሆን በአንድ ሎት ምድብ ለተጠየቁ የስራ ዝርዝሮች ሙሉ በሙሉ ዋጋ መሞላት አለበት።

6. በጨረታ የተሞላው ዋጋ የጨረታ ሠነዱ ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ45 ተከታታይ ቀናት ፀንቶ ይቆያል።

7. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

 ለማንኛውም ተጨማሪ ማብራሪያ

ስልክ ቁጥር ባህር ዳር

058-218-0538 / 09-18-01-06-17 /09-18-71-66-16

አዲስ አበባ – ስልክ ቁጥር 011 126 5338/ 09-18-80-03-64/ 09-11-90-86-29

ዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን