የሰሜን ጎንደር ዞን ገንዘብ መምሪያ ግዥ ንብረት አስተዳደር ቡድን ለ2019 በጀት አመት በዞኑ ስር ለሚገኙት መምሪዎች አገልግሎት የሚውሉ የመኪና መለዋወጫ፣ የመኪና ዘይት እንዲሁም የመኪና ጎማ በግለጽ ጨረታ በሎት አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የሰሜን ጎንደር ዞን ገንዘብ መምሪያ ግዥ ንብረት አስተዳደር ቡድን ለ2019 በጀት አመት በዞኑ ስር ለሚገኙት መምሪዎች አገልግሎት የሚውሉ የመኪና መለዋወጫ፣ የመኪና ዘይት እንዲሁም የመኪና ጎማ በግለጽ ጨረታ በሎት አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Be'kur (Sep 28, 2026)

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የሰሜን ጎንደር ዞን ገንዘብ መምሪያ ግዥ ንብረት አስተዳደር ቡድን ለ2019 በጀት አመት በዞኑ ስር ለሚገኙት መምሪዎች አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1. የመኪና መለዋወጫ፣ ሎት 2. የመኪና ዘይት እንዲሁም ሎት 3. የመኪና ጎማ በግለጽ ጨረታ በሎት አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። 

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

1. የግብር ከፋይ የግብር መለያ ቁጥር (ቲን) የተቀበሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችልና በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ አግባብ ያለው የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ።

2. የዘመኑን ግብር የከፈለበት የግብር ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ።

3. ተጫራቾች የሚጫረቱትን የግዥ መጠን ከብር 500,000 (አምስት መቶ ሽህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።

4. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ ብር 50,000 (ሃምሳ ሽህ ብር)  በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በመ/ቤቱ መሂ 1 በማስያዝ  ጨረታው እስከ ሚዘጋበት ሰዓት ድረስ ግዥ/ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ውስጥ ወይም ከኦርጅናል ጨረታ ሰነዱ ጋር በፖስታ በማሸግ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ይሁን እንጅ የጨረታ ማስከበሪያ ጥሬ ገንዘብ ፖስታ ውስጥ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አይፈቀድም፡፡ ይህ ሳይሆን ቢቀር ወይም የሚያስይዙት ዋስትና  ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ተጫራቹ ከውድድሩ ውጭ ይሆናል።

5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር በማያያዝ በፖስታ ውስጥ በማሸግ ማቅረብ አለባቸው።

6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ከሰ/ጎ/ዞን ፋይናንስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 1 ማግኘት ይችላሉ።

7. ተጫራቾች ሰነዱን ሲሞሉ ሥርዝ ድልዝ የተሞላበት ሳይኖረው ኦርጅናልና ኮፒ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በሰሜን ጎንደር ዞን ገንዘብ መምሪያ ግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 1 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስገባት ይችላሉ።

8. ጨረታው በጋዜጣ የሚቆይበት ጊዜ ከመስከረም 18/2019 እስከ መስከረም 27/2019 ዓ.ም ለ10 ተከታታይ ቀናት ይሆናል።

9. ጨረታ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግዥና  ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 1  መስከረም 28/2019 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ታሽጎ  ከረፋዱ 4፡30 የከፈታል።

10. አሸናፊው ተጫራች አሸናፊ የሆነበትን  እቃዎች  የሚያቀርበው የመኪና መለዋወጫውን በጎንደር ከተማ ጋራጅ አሸናፊ ላይ  እና የመኪና ዘይት እና ቅባት  ለሰ/ጎ/ዞን ንብረት ክፍል  የሚያስረክብ ይሆናል።

11. ተጫራቾች በሚያቀርቡት የማወዳደሪያ ሃሳብ ስማቸውን፣ ፊርማቸውን እና ሙሉ አድራሻቸውን ማስፈር አለባቸው። የጨረታ ውድድር የሚካሄደው በሎት ድምር ይሆናል።

12. የጨረታው መዝጊያ ቀን ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የማወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና እራሳቸውን ማግለል አይችሉም።

13. መስሪያ ቤቱ  ይህንን ጨረታ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ሆኖም ጨረታው በመሰረዙ ተጫራቾች ለመወዳደር ላወጡት ወጭ መ/ቤቱ ኃላፊነት የማይወስድ መሆኑን።

14. የጨረታ መክፈቻ ቀኑ የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።

15. ስለጨረታው ተጨማሪ መረጃ ቢያስፈልጋቸው በስራ ሂደቱ ቢሮ ቁጥር 1 ዘወትር በስራ ሰዓት በአካል ቀርበው ወይም በስልክ ቁጥር 058 417 2544 / 058 417 0126 ደውለው መረጃ መጠየቅ ይችላሉ።

የሰሜን ጎንደር ዞን ገንዘብ መምሪያ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *