Be'kur (Sep 28, 2026)
የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ
በአፈ/ከሳሽ ትእግስት አበባየሁ እና በአፈ/ተከሳሽ ተመስጌን ጌጡ መካከል ስላለው የአፈጻጸም ክስ ክርክር ጉዳይ፤ የአፈ/ተከሳሽ የሆነውን ቤት ካርታ ቁጥር 33422/08 የተመዘገበ ቤት የመነሻ ዋጋውን ሳይጠብቅ 73‚306,003.62 (ሰባ ሶስት ሚሊዩን ሶስት መቶ ስድስት ብር ከስልሳ ሁለት ሳንቲም) በማድረግ ጨረታው ከመስከረም 18/2019 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 17/2019 ዓ.ም ለ30 ቀን በጋዜጣ ታትሞ ቆይቶ፤ ጥቅምት 18/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 6፡00 በጨረታ ይሸጣል። መጫረት የምትፈልጉ በቦታው ተገኝታችሁ መጫረት የምትችሉ ሲሆን። አሸናፊው ወዲያውኑ ¼ኛውን በከፍተኛ ፍርድ ቤት ፀደይ ባንክ አካውንት 0313390000027 በማስያዝ እና ቀሪውን ደግሞ በቀጠሮው ቀን ይዞ እንዲቀርብ ሲል ፍ/ቤቱ አዝዟል።
የአዊ ብሔረሰብ አስ/ከፍ/ፍ/ቤት