የቦታው ስፋት 155.39 ካ.ሜ የሆነ የቤት ሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ – test3.diretenders.com

የቦታው ስፋት 155.39 ካ.ሜ የሆነ የቤት ሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ


Addis Zemen (Sep 29, 2026)

የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

የፍ/ባለመብት እነ አቶ አየለ ዘውዴ እና የፍ/ባለዕዳ እነ ሄርሚላ ከበደ / መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር/93818 በ21/9/2016ዓ/ምእናበኮ/መ/ቁ/103291በ19/3/2017ዓ.ምበፌ/መ/ደ/ፍ/ቤትበኮ/መ/ቁ. 103291 በቀን 1/10/2018ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት ፍርድ ያረፈበት ቤት በቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 4 የሚገኝ በይዞታ መለያ ቁጥር AA000040400900/911 በአበበች መርጊያ ስም የተመዘገበ ይዞታው ውስጥ የቤ/ቁ/365 በሚል የሚታወቅ ቤት እና ቤቶች (6 ክፍል ቤቶች፤ በረንዳ ላይ በቆርቆሮ የተሰራ አንድ ዕቃ ቤት) የቦታው ስፋት 155.39 ካ.ሜ የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 7,550,103 (ሰባት ሚሊዮን አምስት መቶ ሃምሳ ሺህ አንድ መቶ ሦስት ብር) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ጥቅምት 24 ዓ.ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ 5፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።

የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4ኛውን በንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል። ከ1/4ኛው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም። በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም CPO አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት። በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251 11 273 0852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን
የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ / ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *