የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን (አሚኮ)የመዋቢያ ክፍልና ዳይሬክተር ኦፊስ ኢንቴሬር ስራ ደረጃ 8 የህንጻ ማስዋብ ስራ ፍቃድ ያላቸዉ፣ የስቲዲዮ ቢ የኢፖክሲ ስራ ደረጃ 8 የህንጻ ማስዋብ ስራ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸዉን በግልጽ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ አሸናፊዉን በመለየት ማሰራትና መግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን (አሚኮ)የመዋቢያ ክፍልና ዳይሬክተር ኦፊስ ኢንቴሬር ስራ ደረጃ 8 የህንጻ ማስዋብ ስራ ፍቃድ ያላቸዉ፣ የስቲዲዮ ቢ የኢፖክሲ ስራ ደረጃ 8 የህንጻ ማስዋብ ስራ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸዉን በግልጽ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ አሸናፊዉን በመለየት ማሰራትና መግዛት ይፈልጋል


Be'kur (Sep 28, 2026)

በድጋሚ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ ፤ቁጥር 04/2019

የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን (አሚኮ)

  • ሎት1. የመዋቢያ ክፍልና ዳይሬክተር ኦፊስ ኢንቴሬር ስራ ደረጃ 8 የህንጻ ማስዋብ ስራ ፍቃድ ያላቸዉ።
  • ሎት 2. የስቲዲዮ ቢ የኢፖክሲ ስራ ደረጃ 8 የህንጻ ማስዋብ ስራ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸዉን በግልጽ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ አሸናፊዉን በመለየት ማሰራትና መግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ በጨረታዉ መወዳደር ትችላ ላችሁ።

  1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ ለግንባታ ስራዎች የከተማ ልማት የብቃት ምስክር ወረቀት፣የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ሰርተፍኬት ማስረጃ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ፎቶ ኮፒ አድርገው ማያያዝ ይኖርባቸዋል።
  2. ተጫራቾች የሚጫረቱበት ጠቅላላ ድምር ዋጋ 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ) ብር እና ከዚያ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ ሰርተፊኬት ማያያዝ ይጠበቅባቸዋል።
  3. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ሎት1 እና ሎት2 በተከታታይ 21 (ሃያ አንድ ቀናት) እስከ ከቀኑ 11፡30 ድረስ የጨረታ ሰነዱን 500 (አምስት መቶ) ብር አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ቢሮ ቁጥር 106 መግዛት ይቻላል። የፋይናስ ሰነዶችን በመሙላት ኦርጅናል እና ኮፒ በማድረግ በጥንቃቄ በፖስታ በማሸግ የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም፣ ፊርማና አድራሻ በትክክል በመሙላት ለዚህ ሲባል በተዘጋጀዉ የጨረታ ሣጥን ሎት1 እና ሎት2 በ22ኛዉ ቀን እስከ 4፡00 ድረስ ማስገባት አለባችሁ።
  4. ጨረታው ሎት1 እና ሎት2 በ22ኛው ቀን ከቀኑ 4፡00 ይዘጋና በእለቱ ከቀኑ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ ግዥና ንብረት ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክተር 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 104 ይከፈታል። ተጫራቾች ባይገኙም ጨረታው በእለቱ ይከፈታል።
  5. የጨረታ ማስከበሪያ የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ የተመሰከረለት ቼክ ወይም ስፒኦ፣በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል። ይህም ሲባል በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በቢሮው ገንዘብ ያዥ በኩል ደረሰኝ በማስቆረጥ የደረሰኙን ፎቶ ኮፒ ከጨረታው የፋይናንስ ሰነድ ፖስታ ውስጥ ማስገባት አለባችሁ።
  6. ጨረታው የሚከፈትበት ሎት1 እና ሎት2 በ22ኛዉ ቀን 4፡00 ይዘጋና 4፡30 ይከፈታል፤ ቀኑ በዓል ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን 4፡00 ይዘጋና 4፡30 ይከፈታል።
  7. ቢሮው ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  8. የሚፈለጉትን የመዋቢያ ክፍልና ዳይሬክተር ኦፊስ ኢንቴሬር ስራ እና እስቲዲዮ ቢ የኢፖክሲ ስራ፣ ዓይነት ፣ብዛትና ስፔስፍኬሽን እንዲሁም የውል ቃሎች ከሰነዱ ጋር ተዘጋጅቶ የቀረበ መሆኑን እንገልፃለን።
  9. የጨረታ ሰነዱን አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ቀበሌ 13 አየር መንገድ በሚወስደዉ አስፓልት፤ ገጠር መንገድ ከፍ ብሎ ባለዉ ህንጻ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 106 ድረስ በመምጣት መግዛት ይቻላል።
  10. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 320 9735 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን

ባህር ዳር


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *