Be'kur (Sep 28, 2026)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የአማራ ኅብረት ስራ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ፌዴሬሽን ኃላፊነቱ የተወሰነ የፌዴሬሽኑንና የአባል ዩኒዮኖችን የፋይናንስ፣ የቁጠባና ብድር፣ የክፍያ፣ የግብይትና የተቋማዊ አስተዳደር አገልግሎቶች ከወረቀት ነፃ፣ ፈጣን፣ ግልጽ፣ ተጠያቂነት ያለዉ፣ በአንድ የተቀናጀ ኔትወርክ ላይ የሚሰራ ኮር ባንኪንግና ኢአርፒ /Core Banking and ERP/ ሶፍትዌር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም፡-
- በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸዉ እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ።
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸዉ።
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ቫት (ቫት) ከፋይነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች በጨረታዉ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር ከ1-3 የተጠቀሱት እና የሚመለከታቸዉን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከቴክኒካል ስፔስፊኬሽን ሰነዶቻቸዉ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ።
- በጨረታዉ አሸናፊ ሁኖ የሚመረጠዉ በቴክኒክ ግምገማዉ ካለፉ ተጫራቾች መካከል በቀረበዉ ዝርዝር መሰረት በእያንዳንዱ ሎት ጥቅል ድምር ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበዉ ድርጅት ሲሆን በጥቅል ድምር አሸናፊ የሚያልፍባቸዉ ግዥዎች ለአንድም ግዥ ዋጋ አለመሙላት ከጨረታ ዉድድር ዉጭ ያደርጋል።
- ተጫራቾች በፌዴሬሽኑ ዋና ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 222 በመምጣትና የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት የጨረታ ሰነዱን ማግኘት ወይም መግዛት ይችላሉ።
- አሸናፊዉ ክፍያ የሚከፍለዉ ለአንድ አመት የሚቆይ 5 በመቶ ሬቴንሽን ተሰልቶ የሚቆረጥ እና ቀሪዉ ክፍያ በሶስት ጊዜ የሚከፈል ይሆናል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ዋስትና በአማራ ኅብረት ስራ ማህበራት የገንዘብ ቁጠባና ብድር ፌዴሬሽን ስም ማስያዝ አለባቸዉ።
- ማንኛዉም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም በአንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች በማድረግ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በአማራ ኅብረት ስራ ማህበራት የገንዘብ ቁጠባና ብድር ፌዴሬሽን በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ማስታወቂያዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ ቀናት ዉስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛዉ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በአማራ ኅብረት ስራ ማህበራት የገንዘብ ቁጠባና ብድር ፌዴሬሽን በ3፡30 ታሽጎ በ4፡00 ይከፈታል።
- በጨረታዉ አሸናፊ የሆነ አቅራቢ የዉል ማስከበሪያ 10 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይንም በሁኔታ ያልተመሰረተ ዋስትና ማስያዝ እና የአገልግሎት ወጭ ችሎ ማስረከብ አለበት።
- ፌዴሬሽኑ 20 በመቶ ከግዥዉ መጨመር ወይንም መቀነስ ይችላል። የተሻለ አማራጭ ካገኘም ጨረታዉን በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ። በማስታወቂያ ላይ ያልተገለፁ ነገሮች ቢኖሩ በግዥ መመሪያዉ መሰረት ተፈፃሚ ይሆናሉ።
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡-058 320 4082 በመደወል መረጃ መጠየቅ ይችላሉ።
የአማራ ኅብረት ስራ ማህበራት የገንዘብ ቁጠባና ብድር ፌዴሬሽን