የአዳማ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በ2019 ዓ.ም በጀት ለሥልጠና ለቢሮ ውስጥ የሚውል የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የአዳማ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በ2019 ዓ.ም በጀት ለሥልጠና ለቢሮ ውስጥ የሚውል የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Sep 28, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ

የአ/ፖ/ቴ ኮሌጅ በ2019 ዓ.ም በጀት ለሥልጠና ለቢሮ ውስጥ የሚውል የICT እና እስቴሽነሪ መሳሪያዎች የኤሌክትሪክ፣ ፈርኒቸሮች፣ የኮንስትራክሽን ዕቃዎችን፣ የአውቶሞቲቭ፣ ለሆቴል ማሰልጠኛ፣ ለልብስ ስፌት (Garment & Textile)፣ ለውበት ማሰልጠና እቃዎች፣ ለጫማና ቆዳ ማሠልጠኛዎችን በጽዳት መሣሪያዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ

1. በየሥራ መስኩ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፣

2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ወይም ለመክፈላቸው ማስረጃ የሚያቀርብ።

3. የአቅራቢነት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ

4. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ

5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00 /ሃምሳ ሺህ/ በባንክ በተመሰከረ ቼክ (CPO)ማስያዝ አለባቸው።

6. ተጫራቾች የማይመለስ ብር 400.00 /አራት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን በመግዛት በተዘጋጀው ሰነድ ላይ ብቻ ዋጋ በመሙላት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ኮሌጁ ለዚህ ጨረታ ባዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ኦርጅናል እና ኮፒ በማድረግ በሰም በታሸገ በ2 ፖስታ አድርጋችው ማስገባት አለባቸው። ሳጥኑ በ11ኛው ቀን ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዛው ዕለት በ9፡00 ሰዓት ይከፈታል።

7. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ቫት ያካተተ መሆን አለበት። ይህ ካልሆነ የቀረበው ዋጋ ቫት ያካተተ እንደሆነ ተቆጥሮ ይወሰዳል።

8. የጨረታው አሸናፊ በጨረታው ያሸነፈባቸው ዕቃዎች እሰከ በጀት አመቱ መጨረሻ ሲታዘዝ ኮሌጅ ድረስ በራሱ ወጭ ማቅረብና የዕቃው ጥራት በተጠቃሚው ሲረጋገጥ ብቻ ርክክብ የሚደረግና ከፍያ የሚፈጸም ይሆናል፡።

9. ኮሌጁ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የማሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

10. ለተጨማሪ መረጃ ስ.ቁ 022 111 5245 ወይም 09 02 32 28 91 / 09 12 24 96 92 ማነጋገር ይችላሉ።

አድራሻ፡– አዳማ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ አዳማ ከተማ ዳዳቻ አራራ ወረዳ

በኦሮሚያ ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ሥልጠና ቢሮ የአዳማ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ