Addis Zemen (Sep 29, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
ብሔራዊ ግልፅ ጨረታ
የጨረታ ቁጥር LP/OT/03/SIG/2019
1. የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ሜክሲኮ አካባቢ በሚገኘው ፊሊፕስ ህንፃ ላይ ለዋና መስሪያ ቤት አገልግሎት የሚጠቀምበትን ቢሮ ለ2019 ዓ.ም የፅዳት አገልግሎት ግዥ በዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መፈፀም ይፈልጋል።
2 በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ብቁ ተጫራቾች ህጋዊ ለ2018/19 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የዘመኑን ግብር መከፈላቸውን የሚያረጋግጥ በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ከግብር ሰብሳቢው ባለሥልጣን የተሰጠ የምስክር ወረቀት/ የታክስ ክሊራንስ/፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (Tin No) ሠርተፊኬት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት እና የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ወይም ሌላ የሚመለከተው የመንግስት አካል ባዘጋጀው የዕቃ አቅራቢዎች አገልግሎት ሰጪ ዝርዝር ውስጥ መካተታቸውን /መመዝገባቸውን/ የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው።
3. ብቁ ተጫራቾች በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የተሟላ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (ብር አምስት መቶ) በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቁጥር 1000000888862 ገቢ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መክፈቻ ቀን ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት (ከሰኞ እስከ ዓርብ፣ ከሰዓት በፊት ከ2፡00-6፡00 ከሰዓት በኋላ ከ7፡00-11፡00 ቀጥሎ በተመለከተው አድራሻ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ
ግዥና ንብረት አስተዳደር መምሪያ
አድራሻ አዲስ አበባ ልደታ ክ/ከተማ
ጨለለቅ አልሳም ህንጻ ፊት ለፊት
ፊሊፒስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 220
ስልክ ቁጥር +251 11 551 6271
አዲስ አበባ፣ኢትዮጵያ
4. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው በጨረታው መክፈቻ ላይ መገኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በተራ ቁጥር 3 በተገለፀው አድራሻ መስከረም 28 ቀን 2019 ዓ.ም. ከቀነ 8፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከቀኑ 8፡15 ይከፈታል። ዘግይቶ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ የተመሠከረለት የክፍያ ማዘዣ (CPO) ከቴክኒክ መጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
6. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ቢያንስ ለስልሳ (60) ቀናት ፀንቶ የሚቆይ መሆን ይኖርበታል።
7. የጨረታ ዋጋ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለስላሳ (30) ቀናት ይሆናል።
8. ግሩፑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ