Addis Zemen (Sep 29, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ኢኤአ/ፍፋግ/ግጨ-009/2019
ተቋማችን ለምዕራብ አዲስ አበባ ሪጅን ለሠራተኞች የክበብ አገልግሎት የሚሰጥ ድርጅት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
|
ሎት |
የዕቃው ዓይነት |
የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ (CPO) |
የጨረታ መዝጊያ ቀን እና ሰዓት |
የጨረታ መክፈቻ ቀን እና ሰዓት |
|
1 |
ለምዕራብ አ.አ ሪጅን ለሠራተኞች የክበብ አገልግሎት የሚሰጥ ድርጅት ግዥ |
50,000.00
|
ጥቅምት 5 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት |
ጥቅምት 5 ቀን 209 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት |
1, ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራ የዘመኑ ግብር የተከፈለበት የንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ፣ የታደሰ የታክስ ክሊራንስ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል ፤የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለው በጨረታው መሳተፍ ይችላል።
2. ተጫራቾች ዝርዝር መግለጫ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ሜክሲኮ ንብ ባንክ በሚገኝበት ዋናው መስሪያ ቤት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት 10ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው ፍሊትና ፋሲሊቲ ግዥ ክፍል በመምጣት የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000068699332 በመክፈል ሶፍት ኮፒ በኢሜይል አድራሻቸው መውሰድ ይችላሉ።
3. አድራሻ፡- ሜክሲኮ ንብ ባንክ በሚገኝበት ዋናው መስሪያ ቤት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋናው መሥሪያ ቤት 10ኛ ፎቅ ላይ ፍሊትና ፋሲሊቲ ግዥ ክፍል ስልክ ቁጥር 011-156-0148
4. ተጫራቾች ለጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ የሚያቀርቡት የገንዘብ መጠን በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና “ETHIOPIAN ELECTRIC UTILITY” በሚል መሆን ይኖርበታል።
5. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ ከላይ እስከ ተጠቀሰው ቀን፣ ሰዓት እና አድራሻ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፣
6. ጨረታው ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ተዘግቶ በተመሳሳይ ቀን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል።
7. ተቋሙ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት