የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ አስተዳደራዊ ፍርድ ቤት የሆቴል መስተንግዶ አገልግሎት ግዥ /በአዳማ ከተማ/ ባለ 4 ኮከብና ከዛ በላይ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ አስተዳደራዊ ፍርድ ቤት የሆቴል መስተንግዶ አገልግሎት ግዥ /በአዳማ ከተማ/ ባለ 4 ኮከብና ከዛ በላይ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Sep 29, 2026)

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር ECMAT/OT/02/2019

የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ አስተዳደራዊ ፍርድ ቤት ከዚህ በታች የተጠቀሰውን አገልግሎት፡–

1፡– የሆቴል መስተንግዶ አገልግሎት ግዥ /በአዳማ ከተማ/ ባለ 4 ኮከብና ከዛ በላይ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

ስለዚህ ከዚህ በታች የቀረቡትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ያስታዉቃል።

1. በዘርፉ የተሰማሩና የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት (VAT)፣ የግብር ከፋይነት መለያ ሰርተፍኬት (TIN)፣ በጨረታው ለመካፈል የሚያስችላችሁን ማስረጃ (Tax Clearance)፣ አቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ መመዝገቡን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ተወዳዳሪዎች መሆን ይኖርባቸዋል”

2. ተጫራቾች ለጨረታው የተዘጋጀውን ሰነድ የማይመለስ /300.00/ሶስት መቶ ብር/ በመስሪያ ቤቱ የንግድ ባንክ አካዉንት ቁጥር 1000670020308 ላይ በማስገባት መግዛት ትችላላችሁ።

3. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ሰነድ ቴክኒካል ኦርጅናልና ኮፒ፣ፋይናንሽያል ኦርጅናልና ኮፒ በማለት ለይተው ማቅረብ አለባቸዉ

4. ተጫራቾች ከሚያቀርቡት ሰነድ ጋር ለጨረታው ማስከበሪያ ብር 20,000.00፣ ሲ.ፒ.ኦ በEthiopian Capital Market Administrative Tribunal ስም የተጻፈ ማቅረብ አለባቸዉ

5. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ማስታወቂያዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ በሚቆጠር በ11ኛው ቀን የሚከፈት ይሆናል። 11ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል። ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይ በፍርድ ቤቱ አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል፤

6. የጨረታው አሸናፊም ሆነ ተሸናፊ ውጤቱ በጽሁፍ ይገለጽላቸዋል፤

7. ፍርድ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡– ፒያሳ ጣይቱ ሆቴል ጀርባ ከኢትዮ ሴራሚክ ጎን በሚገኘዉ ዋስትና የንግድ ማዕከል ሕንፃ 16ኛ ፎቅ

ስልክ ቁጥር /+251 11 127 5721

የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ አስተዳደራዊ ፍርድ ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *