Be'kur (Sep 28, 2026)
የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ
በአፈ/ከሳሽ ዬሃንስ ገረም እና በአፈ/ተከሳሽ በእነ ጌትነት ዳኛው 2ቱ ራሳቸው መካከል ስላለው የገንዘብ ክስ ክርክር ጉዳይ፤ በአገው ግምጃ ቤት ከተማ አስተዳደር ቀበሌ 02 ፣በምስራቅ፣ በምእራብ እና በደቡብ መንገድ ፣በሰሜን ቴሌኮምኒኬሽን፣ መካከል ተዋስኖ የሚገኘው እና በአቶ ጌትነት ዳኛው ስም
ተመዝግቦ የሚገኘው የድርጅት ቤት በመነሻ ዋጋ ብር 14‚225.136.32 (አስራ አራት ሚሊዩን ሁለት መቶ ሃያ አምስት ሽ አንድ መቶ ሰላሳ ስድስት ብር ከሰላሳ ሁለት ሳንቲም) ሆኖ የመነሻ ዋጋውን ሳይጠብቅ በጨረታ ይሸጣል፡፡ የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ከመስከረም 18/2019 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 18/2019 ዓ.ም ድረስ የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ቆይቶ፤ ጥቅምት 19/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 6፡00 ጨረታው ይካሄዳል፡፡ ተጫራቾች ወደ ጨረታው ስትመጡ የጨረታውን መነሻ ዋጋ ¼ውን በሲፒኦ አስይዛችሁ እንድትቀርቡ ፍ/ቤቱ አዝዟል፡፡
የባንጃ ወረዳ ፍ/ቤት