ፀደይ ባንክ ባሕር ዳር ዲስትሪክት መኖሪያ ቤት መሸጥ ይፈልጋል – test3.diretenders.com

ፀደይ ባንክ ባሕር ዳር ዲስትሪክት መኖሪያ ቤት መሸጥ ይፈልጋል


Be'kur (Sep 28, 2026)

የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ

ተ .ቁ

የተበዳሪው ስም

የንብረት አስያዥ ስም

አበዳሪው ቅ/ፍ

ለጨረታው የቀረበው ንብረት መግለጫ

የጨረታው መነሻ ዋጋ በብር

ጨረታው የሚከናወንበት

ጨረታው የወጣው

አገልግሎቱ

የሚገኝበት አድራሻ

የካርታ ቁጥር

የቦታው ስፋት

ቦታ

ቀን

ሰዓት

1

ትዕግስት ምናለና ጓደኞቻቸው

አቶ ይበልጣል መኮነን

ዶና በር

መኖሪያ

ባ/ዳር ከተማ ማራኪ ቀበሌ

22327/- 2000

150

15,048,916.48

ፀደይ ባንክ ባ/ዳር ዲስትሪክት የስብሰባ አዳራሽ

ጥቅምት 20/2019 ዓ.ም

ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 6፡00

ለመጀመሪያ ጊዜ

2

ቹቹ ኢንዱስትሪያል ትሬዲንግ

አቶ ጌታቸው ወንድሜነህ ባይሌ

ዶና በር

መኖሪያ

ባ/ዳር ከተማ ቀበሌ 13

AM0010- 62103011

210.85

6,575,661.84

ፀደይ ባንክ ባ/ዳር ዲስትሪክት የስብሰባ አዳራሽ

ጥቅምት 20/2019 ዓ.ም

8፡00 እስከ 11፡00

ለመጀመሪያ ጊዜ

3

ወ/ሮ መሰረት አስማማው አሸብር

አቶ ይበልጣል ሙጨ መንግስቱ

አባይ ዳር

መኖሪያ

አዴት ከተማ ቀበሌ 05

ከአገ/112- 390 /12 150

416

5,440,561.82

ፀደይ ባንክ ባ/ዳር ዲስትሪክት የስብሰባ አዳራሽ

ጥቅምት 21/2019 ዓ.ም

ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 6፡00

ለመጀመሪያ ጊዜ

የሐራጅ ደንቦች፡-

  1. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪል የጨረታዉን መነሻ ዋጋ 1/4ኛ ወይም 25 በመቶ በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ሰነድ በፀደይ ባንክ አ/ማ ስም በማሰራት ለጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ።
  2. ከፍተኛ ዋጋ የሰጠዉ ተጫራች የጨረታዉ አሸናፊ ነዉ የሚባለዉ ከባንኩ አሸናፊነቱን ሚገልጽ ደብዳቤ በጽሁፍ ሲደርሰዉ ብቻ ነዉ።
  3. የጨረታ አሸናፊዉ አሸናፊ መሆኑ በደብዳቤ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ቀናት ውስጥ ቀሪዉን ገንዘብ አጠናቅቆ መክፈል ይኖርበታል። ባይከፍል ግን የሐራጁ ዉጤት ተሰርዞ በሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ያስያዘዉ የጨረታ ማስከበሪያ ለባንኩ ገቢ ይሆናል። በተጨማሪም ንብረቱ ድጋሚ ለሐራጅ ሲቀርብ ለሚታየዉ የዋጋ ልዩነት ይጠየቃል፡። ለተሸነፉት ተጫራቾች ግን ያስያዙት ሲፒኦ ወይም ጥሬ ገንዘብ በዕለቱ ይመለስላቸዋል።
  4. የሐራጁ አሸናፊ ወይም ገዥ ከሚገዛዉ ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸዉንም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎችን የሊዝ ክፍያን ጨምሮ፣ ግብር፣ በዋጋዉ ላይ የሚጨመር እሴት ታክስም ካለ፣ ከስም ማዛወሪያ ጋር የተገናኙ ክፍያዎች እና ሌሎች በህግ ገዥ እዲከፍላቸዉ የተወሰኑ ማናቸዉንም ክፍያዎች ይከፍላል።
  5. ተጫራቾች በሀራጁ ለመሳተፍ ሲመጡ መታወቂያ (የቀበሌ፣ ፓስፖርት ወይም ብሔራዊ መታወቂያ መያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራቾች የህግ ሰዉነት የተሰጣቸዉ አካላት ከሆኑ ደግሞ ህጋዊ ሰዉነት ያገኙበትን ዋና የምዝገባ ምስክር ወረቀትና ሐራጁን ለመሳተፍ የቀረበዉ ግለሰብ ስልጣኑን የሚያሳይ በሰነዶች ማረጋገጫ ምዝገባ ጽ/ቤት የፀደቀ መመስረቻ ጽሁፍ፣ ቃለ ጉባዔ፣ ወይም መተዳዳሪያ ደንብ ወይም የዉክልና ሰነድ ይዞ መቅረብ አለበት።
  6. ንብረቱ በገዥዉ ስም እንዲዞር ባንኩ ለሚመለከተዉ መንግስታዊ አካል ደብዳቤ ይጽፋል።
  7. ለሐራጁ የቀረበዉን ንብረት ለመጎብኘት የሚፈልግ ማንኛዉም ተጫራች ከአበዳሪ ቅርንጫፍ ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በመያዝ መጎብኘት ይችላሉ።
  8. ጨረታዉ በሰንጠረዥ ላይ በተጠቀሰዉ ቀን፣ ሰዓት እና ቦታ ተጫራቾች ወይም ተበዳሪ እና ንብረት አስያዥ ወይም ህጋዊ ወኪሉ እና ታዛቢዎች በተገኙበት ይካሄዳል። ነገር ግን ተበዳሪዉም ሆነ መያዣ ሰጪዉ ባይገኙም ጨረታዉ በሌለበት ይካሂዳል።
  9. ንብረቱን በጨረታ አሸንፎ የገዛ ግለሰብ (ድርጅት) የሽያጭ ገንዘቡን ከፍሎ ካጠናቀቀ በኋላ ባንኩ በሚያስቀምጠዉ ቀናት ዉስጥ ንብረቶቹን መረከብ ያለበት ሲሆን በተጠቀሰዉ ጊዜ ዉስጥ ካልተረከበ በንብረቱ ላይ ለሚደርስ ጉዳት ባንኩ ሀላፊነት አይወስድም። ገዥ በተጠቀሰዉ ጊዜ ንብረቶቹን ካልተረከበ ከንብረቶቹ ጋር በተያያዘ ለሚኖር ወጪ ገዥ ሀላፊነቱን ይወስዳል።
  10. በወንድ ስም የተጠቀሰዉ አንቀጽ ለሴትና ህጋዊ ሰዉነት ላላቸዉ ድርጅቶችም ያገለግላል። ቤትና ቦታዉ በሌላ ዕዳ በፍ/ቤት እግድ ያለበት ቢሆንም ባንኩ እግዱን አስነስቶ ስም ንብረቱን ለገዥ ያዛዉራል።
  11. ባንኩ በማንኛዉም ጊዜ እና ምክንያት ጨረታዉን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ።
  12. ለበለጠ መረጃ ፀደይ ባንክ ባሕር ዳር ዲስትሪክት ዘወትር በስራ ሰዓት በአካል እየቀረቡ መጠየቅ ይችላሉ።

ፀደይ ባንክ ባሕር ዳር ዲስትሪክት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *