Addis Zemen (Sep 28, 2026)
የሆቴልና የስልጠና አዳራሽ አገልግሎት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
OMNl Ethiopia በ AMIRP Forward Media Fellowship Program ስር በሚቀጥሉት ሁለት አመታት በ40 ዙር ለሚያካሂዳቸው ተከታታይ የስልጠና፣ የወርክሾፕ እና ተያያዥ ዝግጅቶች በድምሩ ከ1,000 በላይ ተሳታፊዎችን ማስተናገድ የሚችል የሆቴል፣ የስልጠና አዳራሽ እና ተያያዥ የመስተንግዶ አገልግሎት ከብቁ አገልግሎት ሰጪዎች ለማግኘት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መምረጥ ይፈልጋል።
በዚሁ መሠረት፣ ለጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፦
1. የተጫራቾች ብቃት
ተጫራቾች፦
- የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
- የTN ምዝገባ ሰርተፊኬት ያላቸው፣
- የVAT፣ ተመዝጋቢ የሆኑ፣ እና
- ተመሳሳይ የሆቴል፣ የስልጠና ወይም የኮንፈረንስ አገልግሎት የመስጠት ተገቢ ልምድ ያላቸው መሆን አለባቸው።
2. የስልጠና ቦታ መስፈርቶች :-
ለስልጠናዎቹ የሚቀርበው ቦታ ቢያንስ የሚከተሉትን ማሟላት አለበት፦
- ተሳታፊዎችን በምቾት ማስተናገድ የሚችል በቂ ስፋት ያለው የስልጠና አዳራሽ፤
- ለቡድን ውይይቶች፣ ልምምዶች እና ተግባራዊ ስልጠናዎች ተስማሚ የሆኑ አነስተኛ/Breakout አዳራሾች፤
- በቂ የመኪና ማቆሚያ ቦታ ያለው መሆን ይመረጣል።
3. የኢንተርኔትና የቴክኖሎጂ አገልግሎት
- ፈጣን፣ የተረጋጋ እና ብዙ ተጠቃሚዎችን በአንድ ጊዜ ማስተናገድ የሚችል Wi-Fi/internet
- Zoom፣ Microsoft Teams ወይም ተመሳሳይ የቨርቹዋል ስብሰባ መድረኮችን ለመጠቀም ተስማሚ የኢንተርኔት ጥራት፤
- Projector/Screen፣ የድምፅ ማጉያ እና አስፈላጊ የAudio-Visual መሳሪያዎች።
4. የምግብ፣ መጠጥና መስተንግዶ አገልግሎት
የአገልግሎቱ ዋጋ የሚከተሉትን ጨምሮ መቅረብ አለበት፦
- የጠዋት እና የከሰዓት በኋላ ቡና/ሻይ፣ ወተት እና ተያያዥ መስተንግዶ፤
- ምሳ፤
- የታሸገ የመጠጥ ውሃ፤
- እንደአስፈላጊነቱ ሌሎች ተያያዥ የመስተንግዶ አገልግሎቶች።
5. የመጫረቻ ሰነድ ማቅረቢያ
በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን ከአስፈላጊ ህጋዊ ሰነዶች ጋር ከ18/01/2019 ዓ.ም እስከ 22/01/2019 ዓ.ም ድረስ በድርጅቱ ኢሜይል omni-ethio@gmail.com መላከ ይኖርባቸዋል።
6. የአሸናፊ ተጫራች ማሳወቂያ
OMNl Ethiopia የጨረታውን ውጤት እና ያሸነፈውን ተጫራች በኢሜይል ያሳውቃል።
7. የዋጋ ማቅረቢያ
ተጫራቾች ለሚያቀርቡት እያንዳንዱ አገልግሎት፦
- የአንድ ተሳታፊ ዋጋ (unit Cost) ፣
- በተጠበቀው የተሳታፊ ብዛት መሠረት አጠቃላይ ዋጋ (Total Cost) በግልጽ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
8. የዋጋ አቀራረብ
ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ VAT እና Service Chargeን ጨምሮ የመጨረሻ ዋጋ መሆን አለበት።
9. የጨረታ መሰረዝ መብት
OMNl Ethiopia የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ
በስልክ፦ 09 19 19 64 20 / 09 88 13 69 68 / 09 23 16 16 96
የበለጠ መረጃ ለማግኘት ከላይ በተጠቀሱት ስልክ ቁጥሮች ሊያገኙን ይችላሉ።
ኦምኒ ኢትዮጵያ / OMNl Ethiopia