Addis Zemen (Sep 30, 2026)
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
በአብክመ የኦሮ/ብቻን የደዋ ጨፋ ወረዳ ወለዲ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት በከተማው ውስጥ እያሰራ ላለው የኮሪደር ልማት ስራ የሚሆን 3000 ካሬ ቴራዞን በግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ከአሸናፊዎች መግዛት ይፈልጋል።
በዚህም መሰረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን መስፈርቶቹም:-
- በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች የምዝገባ የምስክር ወረቀት (TIN No) አብረው ማያያዝ የሚችሉና ከ 50,000 ብር በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር ሰነድ የያዘ ከኦሮ/ብ/ዞ/ደ/ጨ/ወ/ ወለዲ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት ቢሮ ቁጥር 02 በመቅረብ ከ 20/01/2019 ዓ/ም የማይመለስ 400 /አራት መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በአየር ላይ ከዋለበት ዕለት ጀምሮ ለ7 /ሰባት/ ተከታታይ ቀናት ገዝተዉ በመሙላት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ /ኢንቨሎፕ/ በማሸግ በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡።
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ አየር ላይ ከዋለበት ዕለት ጀምሮ በ8ኛው ቀን ማለትም በ27/01/2019 ዓ/ም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከቀኑ 4፡30 የጨረታ ሳጥኑ ታሽጐ በዚሁ ቀን 4፡40 የሚከፈት መሆኑን እየገለጽን ሆኖም የመክፈቻዉ ዕለት ባዕላት ላይ ከዋለ በሚቀጥለዉ የስራ ቀናት በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
- ተጫራቾች ለሞሉት ለጠቅላላ የጨረታ መጠን ላይ 10%/ፐርሰንት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች ለሚያቀርቡት መረጃ ኦርጅናልና ኮፒ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ለበለጠ መረጃ የተጫራቾችን መመሪያ ላይ መረዳት ይቻላል ወይም በስልክ ቁ. 09 41 82 73 56/ 09 65 07 65 12 / 09 22 92 61 35 መደወልና መጠየቅ ይችላሉ።
- አሸናፊዎች ያሸነፋትን እቃ ደዋ ጨፋ ወረዳ ወለዲ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት ድረስ ማቅረብ አለባቸው። በጨረታ አሸናፊ የሆኑት ተጫራቾች ዉል ካልገቡ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ በሙሉ ለመንግስት ገቢ ይሆናል።
- መ/ቤቱ ጨረታዉን በሎት ያወዳድራል።
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
በአብክመ የኦሮ/ ብ / ዞን የደዋ ጨፋ ወረዳ
ወለዲ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት