የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በኢትዮጵያ ስካይላይት ሆቴል Phase 1 ሕንፃ ውስጥ የሚገኙ 3 የተለያዩ ቦታዎች ላይ ለምርት ማሳያ ቦታ፤ ጌጣጌጥ ወይም የከበረ ድንጋይ መሸጫ እና 2 ሱቆች የሚፈለጉትን ምርት ወይም አገልግሎት መስጫ የሚውሉ ባዶ ቦታዎችን በኪራይ መስራት የሚፈልጉ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በኢትዮጵያ ስካይላይት ሆቴል Phase 1 ሕንፃ ውስጥ የሚገኙ 3 የተለያዩ ቦታዎች ላይ ለምርት ማሳያ ቦታ፤ ጌጣጌጥ ወይም የከበረ ድንጋይ መሸጫ እና 2 ሱቆች የሚፈለጉትን ምርት ወይም አገልግሎት መስጫ የሚውሉ ባዶ ቦታዎችን በኪራይ መስራት የሚፈልጉ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል


Addis Zemen (Sep 30, 2026)

በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር፡-SSNT-T644

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ– በኢትዮጵያ ስካይላይት ሆቴል Phase 1 ሕንፃ ውስጥ የሚገኙ 3 የተለያዩ ቦታዎች ላይ ለምርት ማሳያ ቦታ፤ ጌጣጌጥ ወይም የከበረ ድንጋይ መሸጫ እና 2 ሱቆች የሚፈለጉትን ምርት ወይም አገልግሎት መስጫ የሚውሉ ባዶ ቦታዎችን በኪራይ መስራት የሚፈልጉ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል፡፡

ተጫራቾች በሆቴል እንግዶች ሊፈለጉ የሚችሉ ነገር ግን በአሁኑ ጊዜ በሆቴሉ ግቢ ውስጥ የማይገኙ ሌሎች ምርቶችና አገልግሎቶች ላይ የተሰማሩ መሆን አለባቸው። (የቆዳ ምርቶች፣ ብሔራዊ/ባህላዊ ቀሚሶች፣ የቡቲክ ሱቆች፣ የመጽሐፍ መደብሮች፣ የቡና ምርት ሱቆች፣ ከቀረጥ ነፃ ሱቆች፣ ባንኮች፣ የውጭ ምንዛሬ ቢሮዎች፣ የመዋቢያ ሱቆች፣ የቆዳ እንክብካቤ ሱቆች፣ የውበት ሳሎኖች፣ የመኪና ኪራይ ቢሮዎች፣ ከሆቴል ጋር የተያያዙ ማናቸውም ምርቶችና አገልግሎቶች መሆን የለባቸውም)።

ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው ላይ እንዲሳተፉ ይጋብዛል።

1. ተጫራቾች ፍቃድ ከሚሰጥ ህጋዊ አካል በዘርፉ ለመስራት የታደሰ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ እና በመንግስት ጨረታዎች ለመሳተፍ የሚያገለግል ጊዜው ያላለፈበት ፈቃድ ያላቸው እና ከግብር እዳ ነጻ ስለመሆናቸው ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ መሆንይኖርባቸዋል።

2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት የስራ ቀናት በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የማይመለስ 200.00 ብር/ሁለት መቶ ብር/ በሂሳብ ቁጥር 1000006958277(E-99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር SSNT-T644 በሚል ገቢ በማድረግና የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ ቅጅ (Deposit Slip Copy)፣ የጨረታውን ቁጥርና አይነት እንዲሁም የድርጅቱን ሙሉ አድራሻ ከታች በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ በመላክ የጨረታ ሰነዱን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል በኢሜይል ማግኘት ይችላሉ።

3. በጨረታው የሚካፈል ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ (Bid security) አንድ መቶ ሺ ብር (ብር 100,000) ለሁለቱ ሱቆች (ሱቅ 3 እና 5)፣ አንድ መቶ ሺ ብር (ብር 100,000) ለጌጣጌጥ ወይም የከበረ ድንጋይ መሸጫ ሱቅ እና ሀያ አምስት ሺ ብር (ብር 25,000.00) ለምርት ማሳያ አገልግሎት የሚውል ቦታ በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወይም ምንም አይነት ቅድመ ሁኔታ የሌለው የባንክ ዋስትና በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስም ማስያዝ ይኖርበታል። ከማንኛውም ኢንሹራንስ ተቛም የተገኘ እና ቅድመ ሁኔታ ያለው የባንከ ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም።

4. ጨረታው ከተዘጋበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 120 ቀናት የሚቆይ ይሆናል። አየር መንገዱ ጨረታው የሚቆይበትን ጊዜ እንዲራዘምለት ተጫራቾችን የመጠየቅ መብት አለው፡፡

ተጫራቾች በጨረታው ደንብ መሠረት የመጫረቻ ሠነዳቸውን (ቴክኒካልና ፋይናንሻል) ዋናውን እና ኮፒውን እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያ በተለያየ ኤንቨሎፕ አሽገው ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል ጥቅምት 05 ቀን 2019 ዓ.ም እስከ ጠዋት 4፡30 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው። ጨረታው ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ አበባ ቦሌ በሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና መስሪያ ቤት የጨረታ መክፈቻ አዳራሽ ውስጥ በተመሳሳይ ቀን ጠዋት 5:00 ሰዓት ላይ ይከፈታል።

ለተጨማሪ ማብራሪያ:

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ

ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ

ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል

ስልክ ቁጥር 011-517-8953

ወ/ሮ ጠይሜ ተሰጋ

ኢ–ሜይል: TeymeT@ethiopianairlines.com

አየር መንገዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *