የካፋ ዞን ፋይናንስና መምሪያ በ2019 በጀት ዓመት የተለያዩ እቃዎችን መግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የካፋ ዞን ፋይናንስና መምሪያ በ2019 በጀት ዓመት የተለያዩ እቃዎችን መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Sep 30, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ማስታወቂያ /ግ/ጨ/ቁጥር 03/2019

የካፋ ዞን ፋይናንስና መምሪያ በ2019 በጀት ዓመት በዞን ማዕከል ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚዉሉ የተለያዩ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ተጫራቾች በመጋበዝ እንደሚከተለው በሎት በመከፋፈል እስከ በጀት ዓመቱ ማብቂያ ማለትም እስከ ሰኔ 30/2019 ዓ.ም ድረስ:-

  • ሎት 1. የተለያዩ ደንብ ልብስ ለሦስተኛ ጊዜ የወጣ፣ 
  • ሎት 2 የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ዓመታዊ የቡኖ መፅሔት ህትመት አገልግሎት እና
  •  ሎት 3 ደረጃ 3 የተለያዩ የመኪና ጥገና ጋራጅ አገልግሎትን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ስስዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች፡-

1. ተጫራቾች የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ፣ በጨረታ ላይ እንዲሳተፉ ከገቢዎች ባለስልጣን የተሰጠ የምስክር ወረቀት ማስረጃ፣ የቫት ፣ የቲን ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት እና ሌሎች መረጃዎች ፎቶ ኮፒ አያይዞ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

2. ተጫራቾች ከላይ የተጠቀሱትን መረጃዎች የጨረታ ዶክመንት ሊገዙ ሲመጡ ኦርጅናሉን እና የማይመለስ ፎቶ ኮፒ አቅርበው እንዲመሳከር የማድረግ ግዴታ አለባቸው፡፡

3. በመሆኑም ተጫራቾች ለሁሉም ሎቶች ለእያንዳንዳቸው የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 500.00 /አምስት መቶ ብር/ካፋ ዞን ገቢዎች ባለስልጣን ቅ/ጽ/ቤት ቀርበው በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት ለተከታታይ 15 ቀናት ካፋ ዞን ፋይ/ኢኮ/ል/መመሪያ ግዥ ንብ/አስ/ሥራ ሂደት በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡

4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ CPO (Certified payment order) በጥሬ ገንዘብ እና በቼክ ሎቶች ለእያንዳንዳቸው ብር /80,000.00/ ሰማኒያ ሺህ ብር/በካፋ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ግዥ ንብ/አስ/ ስም በማሰራት ከኦሪጅናል ፋይናንሻል የጨረታ ሰነድ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ ግዴታ አለባቸው፡፡

5. ተጫራቾች በሎት3. የተለያዩ ለመኪና ጥገና ለመወዳደር ደረጃ 3 ፍቃድ እና የዘመኑን የታደሰ የጋራዥ ኢንሹራንስ ማቅረብ አለባቸው፡፡

6. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ ሠነዱ ላይ በመጻፍ በሰም/በሙጫ/ በታሸገ ኤንቨሎፕ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 ተከታታይ ቀናት በካፋ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ግዥ ንብ/አስ/ በመቅረብ ለዚሁ ሥራ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡

7. የጨረታው ሳጥን በ16ኛው ቀን በ3፡30 ሰዓት ታሽጎ በዚያው ዕለት ከጠዋቱ 4፡00 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በካፋ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ይከፈታል፡፡ የጨረታ መዝጊያ እና መክፈቻ ቀን ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡ በመክፈቻው ዕለት የተጫራቾች ወይም ህጋዊ ተወካዮች ያለመገኘት የጨረታ መክፈት ሂደት አያስተጓጉልም:: 15 ተከታታይ ቀናት የተባለው ቅዳሜና እሁድ እንዲሁም በዓላትም ጨምሮ የሚቆጠር ነው የተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ያለመገኘት የጨረታውን የመክፈት ሂደት አያስተጓጉልም፡፡

8. ተጫራቾች ያሸነፉበትን የጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ /performance bond/ ለማስያዝ ፈቃደኛ መሆን አለባቸዉ፡፡ አሸናፊው ድርጅት ከላይ ሎት 1- እና ለሎት 2 የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በሙሉ በራሱ ወጪ ካፋ ዞን ፋይናንስ መምሪያ አቅርቦ የማስረከብ ግዴታ አለበት፡፡

9. ተጫራቾች አሰሪው መጤት ያዘጋጀውን የተጫራቾች መመሪያ/የቴክኒካል/ ዶክመንት መጠይቅ ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።

10 መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡-047 331 1826 በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡
የካፋ ዞን ፋይናንስ መምሪያ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *